1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመንግሥት የሰሞኑ ርምጃ እና አንድምታው

እሑድ፣ ሚያዝያ 7 2010

 አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣን በያዙ በጥቂት ቀናት ውስጥ የተወሰዱት እርምጃዎች ከየአቅጣጫው ልዩ ልዩ አስተያየቶች እየተሰጡባቸው ነው። እርምጃዎቹን በበጎ የሚመለከቱት እንዳሉ ሁሉ በጥርጣሬ የሚከታተሉም አልጠፉም።

https://p.dw.com/p/2w22T
Äthiopien Premierminister Dr. Abiy Ahmed
ምስል Oromia Government Communication Affairs Bureau

የመንግሥት የሰሞኑ እርምጃዎች አንድምታ

ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ልዩ ልዩ ክስተቶች አስተናግዳለች። በተለያየ የሽብር ወንጀል ተከሰው የነበሩ የ114 ተጠርጣሪዎች ክስ ሰሞኑን ተቋርጦ እየተፈቱ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ በተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዲስ አበባ ውስጥ ዳግም የታሰሩ ጋዜጠኞች ፖለቲከኞች እና ጦማርያን የሚገኙባቸው 11 ሰዎች፣ ባህርዳር ተይዘው የነበሩ የዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች እና ጋዜጠኞች የሚገኙባቸው 19 ሰዎች ከአንድ ሳምንት በፊት ተፈተዋል። እስረኞች ይሰቃዩበታል የሚባለው ማዕከላዊ የወንጀል መመርመሪያ ማዕከልም ባለፈው ሳምንት መዘጋቱ ተነግሯል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ባለፉት ሦስት ዓመታት ከፍተኛ ግጭት እና ተቃውሞ ካስተናገዱ ከተሞች ቢያንስ አምቦን ጎብኝተዋል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣን በያዙ በጥቂት ቀናት ውስጥ የተወሰዱት እነዚህ እርምጃዎች ከየአቅጣጫው ልዩ ልዩ አስተያየቶች እየተሰጡባቸው ነው። እርምጃዎቹን በበጎ የሚመለከቱት እንዳሉ ሁሉ በጥርጣሬ የሚከታተሉም አልጠፉም። የሰሞኑ የመንግሥት እርምጃ እና አንድምታዎቹ የዛሬው እንወያይ ርዕስ ነው። በዚህ ርዕስ ላይ የሚወያዩ ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል።ዶክተር በድሉ ዋቅጅራ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር እንዲሁም በግል ጋዜጣና በማህበራዊ ድረ ገጾች የሚጽፉ፣ አቶ ፋንታሁን ብርሀኑ የመግባባት የአንድነት እና ሰላም ማህበር ሃላፊ እንዲሁም አቶ ፍስሀ ተክሌ በዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ  ናቸው ተወያዮቹ።

ሙሉውን ውይይት የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ።

ኂሩት መለሰ