የሕወሓትና የመከላከያ ሚንስቴር አስጥ አገባ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2013ማስታወቂያ
የሕወሓት ጦር አዛዦች ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ ተዋጊዎቻቸዉ ቆቦ ከተማን ጨምሮ የተለያዩ የአማራና የአፋር ክልል አካባቢዎችን መቆጣጠራቸዉን አስታዉቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሚንስቴር ዛሬ እንዳስታወቀዉ ግን መከላከያ ሠራዊት እራሱን ከመከላከል ዉጪ እስካሁን ድረስ መንግሥት ያወጀዉን የተናጥል ተኩስ አቁም እንዳከበረ ነዉ። ይሁንና የመቀሌዉ ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ የሕወሓት የጦር አዛዥ ጠቅሶ እንደዘገበዉ ሕወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች ድል በማግኘቱ የኃይል ሚዛን የበላይነትን አግኝቷል። የመከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ ለአዲስ አበበባዉ ወኪላችን ለስዩም ጌቱ እንደነገሩት የሕወሓት አማራና አፋር ክልል ተቀዳጀሁ ያለዉን ድል «ከሰርጎ ገብ ዘረፋ ያልዘዘ» በማለት አጣጥለዉታል።
ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ/ ስዩም ጌቱ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሠ