1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐጫሉ ቀብር---የቤተሰቦቹ መልዕክት

ሐሙስ፣ ሰኔ 25 2012

ባለስልጣናቱም፣ ባለቤቱም ከያሉበት መልዕክት አስተላልፈዋል።የሐጫሉ አባት አቶ ሁንዴሳ፣ መንግስት የልጃቸዉን ገዳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ ሲማፀኑ፣ ባለቤቱ ደግሞ ለሐጫሉ መታሰቢያ ሐዉልት እንዲቆም ጠይቀዋል

https://p.dw.com/p/3eiS7
Äthiopien Beerdigung Haacaaluu Hundeessaa in Ambo
ምስል Reuters/Oromia Broadcasting Network

የሐጫሉ የቀብር ሥርዓት

ባለፈዉ ሰኞ ማታ በሰዉ እጅ የተገደለዉ ኢትዮጵያዊዉ ወጣት ድምፃዊና የፖለቲካ አቀንቃኝ ሐጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ በትዉልድ ከተማዉ አምቦ ተቀብሯል። አምቦ ስታዲዮም በነበረዉ የሽኝት ሥነ-ሥርዓትም ሆነ እዚያዉ አምቦ በሚገኘዉ እየሱስ ቤተ-ክርስቲያን በተፈፀመዉ የቀብር ሥርዓት ላይ የፌደራልና የኦሮሚያ ከፍተኛ ባለስልጣናት አልተገኙም።የአንድ ወር እመጫት የሆኑት ባለቤቱም መገኘት አልቻሉም።ባለስልጣናቱም፣ ባለቤቱም ከያሉበት መልዕክት አስተላልፈዋል።የሐጫሉ አባት አቶ ሁንዴሳ፣ መንግስት የልጃቸዉን ገዳይ ለፍርድ እንዲያቀርብ ሲማፀኑ፣ ባለቤቱ ደግሞ ለሐጫሉ መታሰቢያ ሐዉልት እንዲቆም ጠይቀዋል።የቀብሩ ሥርዓት በሚፈፀምበት ወቅት ወጣቱ ድምፃዊ አዲስ አበባ መቀበር አለበት በሚሉ ወጣቶችና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል በተፈጠረ ጠብ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።

ስዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ