1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የቤንዚን ማደያ ለመገንባት የተሰጠንን ቦታ መከላከያ የኔ ነው በማለቱ ተጉላልተናል»

ረቡዕ፣ ነሐሴ 29 2011

የማህበሩ አባላት ለዶቼቬለ እንደተናገሩት የቤንዚን ማደያ ለመገንባት የተሰጣቸውን ቦታ መከላከያ የኔ ነው በማለቱ ሥራቸው ተስተጓጉሏል።ለብዙ ወጭ ተዳርገናል እየተንገላታንም እያሉ ነው።ቦታ እንዲያገኙ የፈቀደው እና ድጋፍም ያደረገላቸው የሐረሪ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ መሬቱ ለነርሱ የተሰጠ ለመሆኑ ማረጋጋጫ እንዳለው ለዶቼቬለ DW አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3P0M5
Äthiopien Stadt Harar
ምስል DW/T. Waldyes

«የቤንዚን ማደያ ለመገንባት የተሰጠንን ቦታ መከላከያ የኔ ነው በማለቱ ተጉላልተናል»

 የሐረር ከተማን የትራንስፖርት እና የነዳጅ ችግር ለማቃለል ፍቃድ አውጥቶ  የሚንቀሳቀው«የሐረር ሜትሮ ታክሲ» የተባለው ማሕበር የተሰጠውን መሬት ማልማት እንዳልቻለ አባላቱ አስታወቁ። የማሕበሩ አባላት ለዶቼ ቬለ እንደተናገሩት የቤንዚን ማደያ ለመገንባት የተሰጣቸውን ቦታ መከላከያ የኔ ነው በማለቱ ሥራቸው ተስተጓጉሏል። ለብዙ ወጭ ተዳርገናል እየተንገላታንም እያሉ ነው። ቦታ እንዲያገኙ የፈቀደው እና ድጋፍም ያደረገላቸው የሐረሪ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ መሬቱ ለነርሱ የተሰጠ ለመሆኑ ማረጋጋጫ እንዳለው ለዶቼ ቬለ DW አስታውቋል። የድሬዳዋው ዘጋቢያችን መሳይ ተክሉ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ