1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሆስፒታሉ አቅምና የታካሚዉ ብዛት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2011

ሆስፒታሉ እስካሁን ብዙዎችን ቢረዳም ሕክምና የሚያስፈልጋቸዉ ሕሙማን ቁጥር ከሆስፒታሉ ሐኪሞችና ቁሳቁስ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ በመሆኑ በሺ የሚቆጠሩ ሕሙማን ለበርካታ ዓመታት ወረፋ ለመጠበቅ ይገደዳሉ

https://p.dw.com/p/3I4U9
Cardiac Center-Ethiopia
ምስል DW/S. Muche

የማዕከሉ አቅምና የታካሚዉ ብዛት

አዲስ አበባ ዉስጥ በ2001 የተመሠረተዉ የልብ ሕክምና ሆስፒታል ለበርካታ ሕሙማን በተለይም ለልጆችና ለሕፃናት ቀዶ-ሕክምናን ጨምሮ የተለያዩ የልብ ሕክምናዎችን እየሰጠ ነዉ።«የልብ ማዕከል ኢትዮጵያ» የተሰኘዉ ሆስፒታል ሕክምናዉን የሚሰጠዉ በነፃ ነዉ።ይሁንና ሆስፒታሉ እስካሁን ብዙዎችን ቢረዳም ሕክምና የሚያስፈልጋቸዉ ሕሙማን ቁጥር ከሆስፒታሉ ሐኪሞችና ቁሳቁስ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ በመሆኑ በሺ የሚቆጠሩ ሕሙማን ለበርካታ ዓመታት ወረፋ ለመጠበቅ ይገደዳሉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ እንደዘገበዉ ወረፋ እየጠበቁ ሕይወታቸዉ የሚያልፍ ሕሙማን ቁጥርም ቀላል አይደለም።ሰለሞን ሆስፒታሉን ጎብኝቶ ለዛሬዉ ጤናና አካባቢ ተከታዩን ዝግጅት አጠናቅሮልናል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ