1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የላሊበላ ዐብያተ ክርስቲያናት

ዓርብ፣ ጥር 24 2011

ነዋሪዎቹ የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለDW እንደተናገሩት ጥገናው በፍጥነት ካልተካሄደ አ/ክርስቲያናቱ ሊፈርሱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለን ብለዋል። የከተማዋ ከንቲባ ለDW እንደተናገሩት ዐብያተ ክርስቲያናቱ ከዚህ ቀደም ሲደረግላቸው በነበረ ጥገና እና በተፈጥሮዊ ምክንያቶች ብዙ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

https://p.dw.com/p/3CadB
Bet Giyorgi Felsenkirche von Lalibela in Äthiopien
ምስል picture alliance/Robert Harding World Imagery

የላሊበላ ውቅር ዐብያተ ክርስቲያን ለአደጋ መጋለጥ

 
የላሊበላ ውቅር ዐብያተ ክርስቲያናት የጥገና ሂደት እንዲፋጠን የከተማዋ አስተዳዳሪዎች እና ነዋሪዎች ጠየቁ። ነዋሪዎቹ የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በቦታው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለDW እንደተናገሩት ጥገናው በፍጥነት ካልተካሄደ አብያተ ክርስቲያናቱ ሊፈርሱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለን ብለዋል። የከተማዋ ከንቲባ ለDW እንደተናገሩት ዐብያተ ክርስቲያናቱ ከዚህ ቀደም ሲደረግላቸው በነበረ ጥገና እና በተፈጥሮዊ ምክንያቶች ብዙ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከፕሬዝዳንት ሽታይንማየር ወደ ስፍራው ተጉዞ የነበረው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  በጉዳዩ ላይ የከተማዋን አስተዳዳሪዎች እና ነዋሪዎች አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ