የህወሀት ቃል አቀባይ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 5 2013ማስታወቂያ
ከወራት በፊት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው እና በትጥቅ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ኦነግ ሸኔ በመባይ የሚታወቀው ቡድን ራሱን የትግይ ኃይል ከሚለው ቡድን ጋር ወታደራዊ ስምምነት ማድረጉ የተለያዩ የዜና አውታሮች ዘግበዋል። በተመሳሳይ መንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ በምህጻሩ ህወሃት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ድርጅታቸው ኢትዮጵያን ካለችበት ቀውስ ለማውጣት ኦነግ ሸኔን ጨምሮ ከሌሎች ድርጅቶችም ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ለዶቼ ቨለ ገልጸዋል። አቶ ጌታቸውን በሳተላይት ስልክ አማካኝነት ስቱዲዮ ከመግባታችን አስቀድሞ አግኝቼ ወቅታዊ ጉዳዮችንም አንስቼላቸዋለሁ።
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ