1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

'የሀገር መድህን ሸንጎ' እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ

ሰኞ፣ መስከረም 11 2013

ራሱን የኢትዮጵያ ፌደራሊት ሐይሎች ጥምረት ብሎ የሚጠራው የሀያ ገደማ ፓርቲዎች ስብስብ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮች ለመፍታት ሁሉም ሐይሎች ያሳተፈ «የሀገር መድህን ሸንጎ» እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ፡፡ የጥምረቱ ሊቀ መንበር ጨምሮ ሌሎች ፓርቲዎች ያሉበት የፌደራሊት ሐይሎች ጥምረት መግለጫ ጥምረቱ አይወክልም ሲል ተቃውሞው ይገልፃል፡፡

https://p.dw.com/p/3inkk
20.06.2013 DW Online Karten Basis Aethiopien spanisch

አደጋ ከደቀኑ ችግሮች ለመዳን 'የፖለቲካ እስረኞች'  ተፈተው፣ ሁሉም ሀይሎች ያካተተ ንግግር ይጀመር

ራሱን የኢትዮጵያ ፌደራሊት ሐይሎች ጥምረት ብሎ የሚጠራው የሀያ ገደማ ፓርቲዎች ስብስብ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ችግሮች ለመፍታት ሁሉም ሐይሎች ያሳተፈ «የሀገር መድህን ሸንጎ» እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ፡፡ ባለፈው ዓመት በመቐለ የተመሰረተውና አሁን ላይ ለሁለት ተከፍሎ ውዝግብ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ፌደራሊስት ሐይሎች ጥምረት ሀገራዊ ምርጫ አለመካሄድና ጨምሮ በኢትዮጵያ በርካታ ዴሞክራስያዊና ሰብአዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመ ነው የሚል ሲሆን በሀገሪቱ መፃኢ ላይ አደጋ ከደቀኑ ችግሮች ለመዳን 'የፖለቲካ እስረኞች'  ተፈተው፣ ሁሉም ሀይሎች ያካተተ ንግግር እንዲጀመር ጠይቋል፡፡ በተጨማሪም የውጭ የፀጥታ ሐይሎች በኢትዮጵያ መኖራቸው ጠቅሶ በተለይም የኤርትራ መንግስት የፀጥታ ሐይሎች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ሲል የኢትዮጵያ ፌደራሊስት ሐይሎች ጥምረት ጥሪ አቅርቧል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የጥምረቱ ሊቀ መንበር ጨምሮ ሌሎች ፓርቲዎች ያሉበት የፌደራሊት ሐይሎች ጥምረት መግለጫ ጥምረቱ አይወክልም ሲል ተቃውሞው ይገልፃል፡፡

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ