1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ንግድ

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ 14 ሺህ ሰራተኞችን በጊዚያዊነት አሰናበተ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 22 2012

የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ አስራ አራት ሺህ ሰራተኞቹን ከዛሬ ጀምሮ ወርሃዊ ክፍያቸው እንደተጠበቀ በጊዚያዊነት ከስራ እንዲሰናበቱ መደረጉን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3aGuV
Äthiopien Hawassa Industrial Park
ምስል AFP/E. Jiregna

የኮሮና ተኅዋሲ ስጋት የተዘጋዉ የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ

የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ አስራ አራት ሺህ ሰራተኞቹን ከዛሬ ጀምሮ በጊዚያዊነት ከስራ ማሰናበቱን አስታወቀ። ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱት ቀደምሲል በአሜሪካና በአውሮፓ ገበያዎች የምርቶቹ ዋነኛ ተቀባይ የነበሩት ድርጅቶች በኮሮና ተህዋስ ወረርሽኝ ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ ነው ተብሏል ። በሌላ በኩል እዛው ሀዋሳ ውስጥ የኮረናን ተህዋስን ለመከላከል በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ የኬሚካል ርጭት ሲካሄድ ውሏል። የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 14 000 ሰራተኞቹን ከዛሬ ጀምሮ በጊዚያዊነት ከስራ ማሰናበቱን አስታወቀ።
የፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ ዛሬ ለዶቼ ቬለ ( DW ) አንዳሰታወቁት ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱት  ቀደምሲል በአሜሪካና በአውሮፓ ገበያዎች የምርቶቹ ዋነኛ ተቀባይ የነበሩት ድርጅቶች በኮሮና ተህዋሲ ወረርሽኝ ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ ነው።
አቶ ፍጹም በማያያዝም << በአሁኑ ወቅት በኢንዱስትሪያል ፓርኩ ከሚገኙት ሃያ ሁለት አምራች ኩባንያዎች መካከል ስምንቱ ምርታቸውን መላክ እንዲያቆሙ የወጪ ምርቶችን ተቀባይ ከሆኑት ድርጅቶች በተገለጸላቸው መሰረት የምርት ስራቸውን በጊዜያዊነት ለማቋረጥ ተገደዋል። በእነኝሁ ኩባንያኛዎች ውስጥ ተቀጥረው በማገልገል ላይ የነበሩ አስራ አራት ሺህ ሰራተኞችም ከሙሉ የደሞዝ ክፍያቸው ጋር ከአስራ አምስት እስከ ሃያ ሁለት ለሚደርሱ ቀናት በጊዜያዊነት እንዲያርፉ ተደርጓል ። በኮሮና ተህዋስ ምክንያት የተስተጓጎለው የአሜሪካና የአውሮፓ ገበያ ሲስተካከል ተመልሰው ወደ ስራቸው የሚገቡ ይሆናል  >> ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የፓርኩን ሰራተኞች ከኮሮና በሽታ ጥቃት ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶች መስጠትንና ከውጭ አገራት የሚመጡ የፓርኩ ሰራተኞች ለአስራ አራት ቀን ተለይተው እንዲቆዩ ማድረግን ጨምሮ የተለያዩ ጥረቶች በመደረግ ላይ እንደሚገኙም አቶ ፍጹም ተናግረዋል ።
በአንዳንድ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የኢንዱስትሪያል ፓርኩ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል በሚል በመሰራጨት ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን የጠቀሱት የፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ ቀሪዎቹ አስራ አራት ኩባንያዎች አሁንም በምርት ስራ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
ከሶስት ዓመት በፊት የምርት አገልገሎት የጀመረው የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በአሁኑ ወቅት ከሰላሳ አራት ሺህ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች የስራ እድል መፍጠሩን ከፓርኩ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በፓርኩ ሃያ ሁለት ኩባንያዎች የማምረቻ ቬድ ወስደው በሙሉ እና በከፊል የተጠናቀቁ የአልባሳት ምርቶቻቸውን ለአገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እያቀረቡ ይገኛሉ።
ከእነኝሁ ኩባንያዎች መካከል በአለም አቀፍ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የግማሽ ምዕተ ዓመት ልምድ ያላቸው የካንቤቢ ዳይፐር አምራቹ ኦን ቴክስ ኩባንያ፣ የአሜሪካው ፒቪ ኤች እና የህንዱ ሬይመንድ ይገኙባቸዋል።

Äthiopien Hawassa Industrial Park
ምስል AFP/E. Jiregna
Äthiopien | Coronavirus | Hwassa Industrial Park, Entlassungen
ምስል DW/S. Wegayahu


ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ