1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የUSAID የ 6 ዓመታት ስራዎች እና ዉጤታቸዉ

ዓርብ፣ ሐምሌ 22 2014

ፕሮጀክቱ በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት በንጽህና እና በጤና ላይ ትኩረት ሰጥቶ በሴቶች እና ህፃናት ላይ ሲሰራ የቆየ ነው የአሜሪካ ግብረሰባይ ድርጅቶች USAID AND SAVE THE CHELDREN በ2016 በ 79 ሚልየን የአሜሪካን ዶላር በማውጣት የጀመሩት ሰራ ነው።

https://p.dw.com/p/4ErZf
Äthiopien Die Chefin von USAID  Samanta Power
ምስል Seyoum Getu/DW

ፕሮግራሙ ህብረተሰቡን በማስተማር እና በማብቃት ትልቅ እገዛ አድርጎዋል

ፕሮጀክቱ በተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት በንጽህና እና በጤና ላይ ትኩረት ሰጥቶ  በሴቶች እና ህፃናት ላይ ሲሰራ የቆየ ነው  የአሜሪካ ግብረሰባይ ድርጅቶች USAID AND  SAVE THE CHELDREN  በ2016 በ 79 ሚልየን  የአሜሪካን ዶላር በማውጣት የጀመሩት ሰራ ነው።

በኢትዮጵክያ ከመንግስት ተቁዋማት ከጤና  ሚንስትር ከግብርና ሚንስትር  እና  ከትምህርት ሚንስትር ጋር በጋራ በመሆን ሲሰራ የቆየው ይህ ፕሮጀክት  በ6 ክልሎች የስራዐተ ትምህርት  እድገት የተመጣጠነ  ምግብን መሻሻል  የህፃናት መቀንጨርን የንጽህ ውኃ አቅርቦት እንደዚሁም የምግብ ስብጥርን ለገበሪው ላማስተማር ታቅዶ የተጀመረ  ነው።

ከተለያዪ ኣካላት ጋር  በትብብር ሲሰራ  የቆየው የስርዐተ ምግብ ትምህርት እድገት  ፕሮጀክት ከ 6 ዓመት በፊት ሲጀመር   በአራት የአርሶ አደር ክልሎች 100 ወረዳዎችን ለማዳረስ ታቅዶ የነበረ ሲሆን ሲጠናቀቅ  1.3 ሚልየን እናቶችን 8.2 ሚልየ ህፅናትን በ6 ክልሎች እና በ 120 ወረዳዎች  አዳርሶዋል ተብሎዋል። በፕሮጀክቱ ማዝጊያ ላይ የተገኙት የጢና ሚንስትር ተወካይ ለDW እንደገለጡት የብሄራዊ የስርዐተ ትምህርትን ፕሮግራምን መሰረት አድርጎ ከዛሪ 6 ዓመት በፊት የተጀመረው ይህ ፕሮግራም ወደ መሪት ወርዶ ህብረተሰቡን በማስተማር እና በማብቃት ትልቅ እገዛ አድርጎዋል ብለዋል።

ይህ ፕሮጀክት የስራተ ምግብ ተግዳሮቶች ናቸው በሚባሉት በቂ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት  መሰረታዊ የጢና እና የምግብ አቅርቦት ከንጽህና ጋር በተያየዘ ደግሞ ከንጹህ ውሀ አቅርቦት እና ንጽህናን ከመጠበቅ ጋር  በማህበረሰቡ ዘንድ መሰረታዊ ለውጥ እና ግንዛቤ እንዲፈጠር አስችሎዋል  ይላሉ ። በፕሮግራሙ ላይ በፕሮጀክቱ ታቅፈው ስራ በመጀምር እራሳቸውን የቻሉ እና ለሎችም ምሳሌ የሆኑ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍልየሚኖሩ ግለሰቦች ተሞክሮም ቀርብዋል።      

በፓናል ውይይት ወቅት ከ 6ቱም ክልሎች የመጡ ተወካዪች በየአካባቢያቸው ያነበረውን የስራ ሂደት ተናግረው የነበረባቸውንም ተግዳሮት ገልጸዋል ፕሮጀክቱ ቢጠናቀቅም እስካሁን ያገኙትን እውቀት በመጠቀም ባፈሩት ባለሙያ ስራው በየክልሉ ባለድርሻ አካላት እንደሚቀጥል እስታውቀዋል። USAID በ79 ሚልየን የአሚሪካን ዶላር ሲሰራ የቆየው ፕሮጀክት መዝጊያ ስነስራት ላይ የተለያዪ ግብረሰናይ ድርጅቶች አመራር እና የሚመላከታቸው ሀላፊዎች የየክልሉ የፕሮጀክት ተሳታፊዎችየተገኙ ሲሆን  USAID  የኢትዮጵያ ዋና ዳይሪክተር ሀገራቸው እና ህዝባቸው በኢትዮጵያ በስኬት ተጠናቀቀው ፕሮጀልት ላይ መሳተፋቸው እንዳደሰታቸው ተናግረዋል።

ሃና ደምሴ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ