1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥት የ2016 ዓ.ም በጀት

እሑድ፣ ሐምሌ 2 2015

መንንግሥት በሚቀጥለው ዓመት አዲስ ቅጥር እንደማይፈጽም ከዚህ ቀደም አስታውቋል። በሌላ በኩል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስተባባሪነት ይገነባሉ የሚባሉ ፕሮጀክቶች ገንዘብ ምንጭ ፣አጠቃቀሙና ኦዲት አያውቃቸውም መባሉ ምክርቤቱን ካነጋገሩ ጉዳዮች አንዱ ነበር።

https://p.dw.com/p/4Tcy5
Äthiopien Volksrepräsentantenhaus
ምስል Solomon Muchie/DW

የ2016 ዓ.ም በጀትና አነጋጋሪዎቹ ፕሮጀክቶች

የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሐሙስ የ2016 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትን  በጀት አጽድቋል። ምክርቤቱ ለመጪው ዓመት ያጸደቀው የ801.6 ቢልዮን ብር በጀት ከአምናው በ1.9 በመቶ ከፍ ያለ ነው።  መንግሥት በዓመቱ ለእዳ ክፍያ ለተፈናቃዮች ሰብዓዊ ድጋፍ ለመልሶ ማቋቋምና ለማዳበሪያ ግዥ ከፍ ያለ በጀት ተመድቧል። በአንጻሩ ለመንገድ ስራ እና ለትምህርት እንዲሁም  ለሌሎችም ዘርፎች ለሚቀጥለው ዓመት የተመደበው በጀት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር ዝቅ ያለ ነው። መንንግሥት በሚቀጥለው ዓመት የሥራ ቅጥር እንደማይፈጽም ከዚህ ቀደም አስታውቋል። በሌላ በኩል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስተባባሪነት ይገነባሉ የሚባሉ ፕሮጀክቶች ገንዘብ ምንጭ ፣አጠቃቀሙና ኦዲት አያውቃቸውም መባሉ ምክርቤቱን  ካነጋገሩ ጉዳዮች አንዱ ነበር። የ2016 ዓ.ም. በጀት ፣ ጉድለቱ ምደባውና አነጋጋሪዎቹ ፕሮጀክቶች እንወያይ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው። በውይይቱ ዶክተር መሠረት ሞላ በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የደቡብ ጎንደር ዞን የጉና በጌምድር ወረዳ ተወካይ እንዲሁም ጋዜጠኛ ሳምሶን ብርሃኔ የሪፖርተር እንግሊዘኛ ክፍል ሃላፊ እና የኤኮኖሚ የቢዝነስና የፋይናንስ ጉዳዮች ዘጋቢ ተሳትፈዋል። ተሳትፈዋል።ሙሉውን ውይይት ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ  

ኂሩት መለሰ