1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሊዎናርዶ ዳቬንቺ ሥራዎች

ሐሙስ፣ ግንቦት 1 2011

ሥነ ጥበብ፤ ሳይንስ፤ ምሕድስና እና ምርምርን አጣምሮ የተካነበት ኢጣሊያዊዉ የትንሣኤ ዘመን ማለትም የሬናይሰንስ ዘመን ዕዉቅ ሠዓይ ሊዎናርዶ ዳቬንቺ የሞተበት 500ኛ ዓመት ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/3IF3v
Leonardo da Vinci 500.Todestag
ምስል DW/H. Tiruneh

የሊዎናርዶ ዳቬንቺ 500ኛ ሙት ዓመት

 በተለይ ዳቬንቺ በተወለደባት ኢጣሊያና በሞተባት ፈረንሳይ ሥራዎቹን፣ የግል ታሪኮቹንና አኗኗሩን የሚዘክሩ አዉደ ርዕዮች ለጎብኚዎች ተከፍተዋል። እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ሚያዚያ 15 1452 የተወለደዉ ዳቬኒቺ ያረፈዉ ግንቦት 2፣ 1519 ዓ,ም ነበር። ያረፈበት ዕለት ባለፈዉ ሳምንት ሲዘከር የፈረንሳይ እና የኢጣሊያ ፕሬዝደንቶች የዳቬንቺን መካነ-ቀብር ጎብኝተዋል። የዛሬዉ የባሕል መድረክ ዝግጅታችን የዳቬንቺን ሥራዎች ባጭሩ ይቃኛል። የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነሕ አጠናቅራዋለች።

ሃይማኖት ጥሩነሕ

ነጋሽ መሐመድ