1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የትራፊክ አስተናባሪዎች

ማክሰኞ፣ ግንቦት 16 2014

ታዳጊ ፍሬዘር ታምራት እና መድሃኒት ማርክነህ በሀዋሳ ከተማ የትራፊክ እንቅስቃሴን በማስተናበር ተማሪዎች ከተሽከርካሪ አደጋ እንዲጠበቁ በማድረጋቸው ደስተኞች መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ‹‹ በትምህርት ቤቶች የመግቢያና የመውጫ ሠዓት ላይ የማስተናበር አገልግሎት በምንሰጥበት ወቅት የሚያበረታቱን ሰዎች የመኖራቸውን ያህል የሚሰድቡንም አሉ ›› ይላሉ ተዳጊዎቹ ፡፡

https://p.dw.com/p/4BmQQ

ሁለቱም የ8ኛ ክፍል ተማሪና የ 15 ዓመት ታዳጊዎች ናቸው። ፍሬዘር  ይህንን የበጎ ፍቃድ ስራ ስለመጀመሯ ለቤተሰቦቿ የነገረችው ከጊዜ በኋላ ሲሆን መድሃኒት  ደግሞ ቤተሰቦቼ መጀመሪያ ላይ እንዳትሰሪ ብለውኝ ነበር ትላለች። ይህም ቤተሰቦቻቸው ለልጆቻቸው ካላቸው ስጋት አንፃር ነው። ታድያ ተማሪዎቹ ወላጆቻቸውን እንዴት አሳመኗቸው?

ዘገባ ፡ ሊሻን ዳኜ
ካሜራ ፡ ሸዋንግዛው ወጋየሁ