1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: "ተፈጥሮን እንንከባከብ በኢትዮጵያ"

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 7 2014

ልእልና ኃይሉ የ13 ዓመት ታዳጊ ናት።ታዳጊዋ ተፈጥሮን እንንከባከብ በኢትዮጵያ Nature Lovers of Ethiopia የተባለ የተፈጥሮ ተንከባካቢ ንቅናቄ መስራች እና መሪ ናት። መሰል ዝንባሌ ያላቸውን 10 ተማሪዎች ከጎኗ በማድረግ ንፁህ አካባቢን የመፍጠር እንቅስቃሴ እያደረገች ትገኛለች። #GOGREENTOBREATHCLEAN” በሚል መርህ ዓለምአቀፍ የአካባቢና አየር ብክለት ጉዳዮች ላይ እውቀት የማስጨበጥ ስራም ትሰራለች::

https://p.dw.com/p/44NSL

ልእልና ታዳጊ ተማሪ ጓደኞቿ ጋር የአትክልት ቦታ እንክብካቤን፣ ታዳሽ ቁሶችን የመፍጠር እንዲሁም ትምህርት ቤቶችን ማፅዳትን የመሳሰሉ ተግባራትን ይሰራሉ። በዚህም እሷ የምትማርበትን ጨምሮ ሌሎች 9 ትምህርት ቤቶች ልእልናን እንቅስቃሴ አምነውበት ተቀላቅለዋታል።
ዘገባ: ሱሙያ ሳሙኤል
ቪዲዮ: ሰለሞን ሙጬ