1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዘረኝነት በኢጣሊያ

ሐሙስ፣ ነሐሴ 24 2010

የኢጣሊያን የሐገር አስተዳደር የሚንስትርነት ሥልጣን የያዙት የአክራሪዉ ተጣማሪ መንግሥት መሥራች ማቲዮ ሳልቫኒ ጥቃቱን ለማስቆም መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ስደተኞ እና የዉጪ ተወላጆችን ተጠያቂ ማድረጋቸዉ ዘረኞች በመንግሥት ባለሥልጣናት ሳይቀር ለመደገፋቸዉ አብነት ሆኗል

https://p.dw.com/p/342hl
Italien Anti-Rassismus-Demo eine Woche nach Schüssen auf Schwarze in Macerata
ምስል Getty Images/AFP/M. Bertorello

(Beri.Berlin) Rassismus in Italien - MP3-Stereo

ኢጣሊያ ዉስጥ በስደተኞች እና በዉጪ ሐገር ተወላጆች ላይ የሚፈፀመዉ የዘረኝነት ግድያ፤ድብደባ እና ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነዉ።ታዛቢዎች እንደሚሉት ሊጋ ኖርድ እና አምስት ኮከብ የተባሉት ቀኝ ፅንፈኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመሠረቱት ተጣማሪ መንሥት በዉጪ ተወላጆች ላይ የሚያራምደዉ የጥላቻ መርሕ የዘረኞቹን ጥቃት እያበረታታ ነዉ።የኢጣሊያን የሐገር አስተዳደር የሚንስትርነት ሥልጣን የያዙት የአክራሪዉ ተጣማሪ መንግሥት መሥራች ማቲዮ ሳልቫኒ ጥቃቱን ለማስቆም መፍትሔ ከመፈለግ ይልቅ ስደተኞ እና የዉጪ ተወላጆችን ተጠያቂ ማድረጋቸዉ ዘረኞች በመንግሥት ባለሥልጣናት ሳይቀር ለመደገፋቸዉ አብነት ሆኗል።ሊዛ ቫይስ የዘገበችዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።

ሊዛ ቫይስ

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ