1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፍ ርዳታ ለቤይሩት መቋቋምያ

ሰኞ፣ ነሐሴ 4 2012

ከኤኮኖሚና ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተደምቶ የሊባኖስን ኤኮኖሚ ያሽመደመደዉ የቤይሩት ፍንዳታ ዉድመትን ለመታደግ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ርዳታ እየላከ ነዉ። የአዉሮጳ ኅብረት ለሊባኖስ መቋቋምያ 33 ሚሊዮን ይሮ የአስቸኳይ ርዳታ ልኮአል። ሃገራቱም የበኩላቸዉን ሰብዓዊ ርዳታ እንዲለግሱ የኅብረቱ ካዉንስልና የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንቶች ጥሪ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/3gjiW
Libanon Folgen der Explosion im Hafengebiet von Beirut
ምስል Reuters/H. McKay

ዓለም አቀፍ ርዳታ ለቤይሩት መቋቋምያ

ከኤኮኖሚና ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተደምቶ የሊባኖስን ኤኮኖሚ ያሽመደመደዉ የቤይሩት ፍንዳታ ዉድመትን ለመታደግ ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ርዳታ እየላከ ነዉ። የአዉሮጳ ኅብረት ለሊባኖስ መቋቋምያ 33 ሚሊዮን ይሮ የአስቸኳይ ርዳታ የላከ ሲሆን የኅብረቱ አባል ሃገራትም የበኩላቸዉን ሰብዓዊ ርዳታ እንዲለግሱ የኅብረቱ ካዉንስልና የኮሚሽኑ ፕሬዚዳንቶች ጥሪ አቅርበዋል። ሊባኖስ የቀድሞ ቀን ገዢ ፈረንሳይ በበኩልዋ በርዳታዉ ቀድማ ተገኝታለች። 

በከፍተኛ ቀዉስ የምትገኘዉ እና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተስፋፋባት ሊባኖስ፤ ከቤይሩቱ ፍንዳታ ዉድመት ብቻዋን ትወጣዋለች ተብሎ አይጠበቀም። ዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ 
በቤይሩት በተከሰተው ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ መሞቱን የኢትዮጵያ መንግሥት አረጋገጠ። ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን የኢትዮጵያ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል። በሊባኖስ የከፋ ቀውስ በፈጠረው ፍንዳታ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 154 መድረሱን የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ከሟቾች መካከል አንዱ ኢትዮጵያዊ መሆኑን አረጋግጠዋል። አምባሳደር ዲና እንዳሉት ሌሎች ዘጠኝ ሰዎች ቆስለዋል።
አምባሳደር ዲና "በእኛ {በኢትዮጵያ} ቆንስላ አማካኝነት በተደረገው ክትትል እና ባገኘንው ሪፖርት አንድ ሰው ነው የሞተው። ሌሎች ዘጠኝ የሚሆኑ ሰዎች ከባድ እና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው አብዛኞቹ የታከሙበት ኹኔታ ነው ያለው። ነገር ግን በሶስት የተለያዩ ካምፖች ካሉ ዜጎቻችን መካከል አንዳቸውም እንዳልተጎዱ፤ ከካምፕ ውጪ ሌሎችም ይኖራሉ ተብሎ ስለሚገመት የቆንስላ ጽህፈት ቤቱ አሁንም ክትትል እያደረገ ነው" ሲሉ ተናግረዋል። 
የሊባኖስ ዜና አገልግሎት ዛሬ እንደዘገበው የአገሪቱ የጤና ምኒስትር ሐማድ ሐሳን በፍንዳታው እስካሁን 154 ሰዎች እንደሞቱ ተናግረዋል። ምኒስትሩ በፍንዳታው ጉዳት ከደረሰባቸው 5,000 ሰዎች አብዛኞቹ ሆስፒታል መግባታቸውንም ተናግረዋል። 120 ሰዎች ደግሞ በአስጊ ኹኔታ ውስጥ ይገኛሉ።
ባለፈው ማክሰኞ ማምሻ በቤይሩት በተከሰተው ፍንዳታ በከተማዋ የሚገኝ ወደብ፣ የእህል እና ልዩ ልዩ ሸቀጦች መጋዘኖች፣ ምግብ ቤቶች እና መደብሮች ወድመዋል።  ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን እንዳለው የከተማዋ ትልቁ የኩላሊት እጥበት የሕክምና ማዕከል፣ መድሐኒቶች እና ክትባቶች የተከማቹባቸው መጋዘኖች ጭምር ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚሼል ኦውን በፍንዳታው መነሾ ላይ በሚደረገው ምርመራ የውጭ ኃይሎች እጅ ይኖርበት እንደሁ እንደሚጣራ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ “የፍንዳታው ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። በሮኬት፣ በቦምብ ወይም በሌላ መንገድ የውጭ ጣልቃ ገብነት ሊኖር ይችላል» ብለዋል። 

አዜብ ታደሰ 
ገበያዉ ንጉሴ