1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉባኤ

እሑድ፣ የካቲት 8 2012

በጀርመን ሙኒክ ከተማ ከትናንት በስቲያ የተጀመረዉ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት በሊቢያ ጉዳይ ሲመክር ዉሏል። ምክክሩ የበርሊን -ሊቢያ ስብሰባ ከተካሄደ ከአንድ ወር በኃላ ዛሬ በሰሜን አፍሪቃዊቷ ሀገር ሊቢያ ቀዉስ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ ዉሎአል። በዓለም ፖለቲካ የአዉሮጳ ተፅኖ ፈጣሪነትም ሌላዉ ርዕስ ነበር።

https://p.dw.com/p/3XrUw
MSC Münchner Sicherheitskonferenz Follow-up Komitee zu Libyen
ምስል picture alliance/dpa

በጀርመን ሙኒክ ከተማ ከትናንት በስቲያ የተጀመረዉ ዓለም አቀፍ የፀጥታ ጉባኤ በዛሬዉ ዕለት በሊቢያ ጉዳይ ሲመክር ዉሏል። ምክክሩ የበርሊን -ሊቢያ ስብሰባ ከተካሄደ ከአንድ ወር በኃላ ዛሬ በሰሜን አፍሪቃዊቷ ሀገር ሊቢያ ቀዉስ ላይ አፅንኦት ሰጥቶ ዉሎአል።  በጉባኤዉ የጀርመን ፌዴራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀይኮ ማስ ቀደም ሲል በርሊን በተካሄደው የሊቢያ ስብሰባ ላይ ተሳታፊ ከነበሩ ሀገራትና ሌሎች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በሊቢያ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል። በጥር ወር በርሊን በተካሄደዉ  የሊቢያ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት አስራ ሁለቱ ሀገራት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሊቢያ ላይ የተጣለዉን የጦር መሳሪያ እገዳ ገቢራዊ ለማድረግ ቃል መግባታቸዉን የጀርመኑ የዉች ጉዳይ ሚኒስትር ሃይኮ ማስ ዛሬ በጉባኤዉ ላይ አስታዉቀዋል። በጀርመን የፌደራል መንግስትና በተባበሩት መንግስታት ባቫሪያ ሙኒክ ላይ እየተካሄደ ባለዉ እና ዛሬ በሚጠናቀቀዉ ጉባዔ ላይ የተባበሩት መንግስታት የሊቢያ ልዩ መልዕክተኛ ጋሳን ሳላሚ በጤና እክል ምክንያት አለመገኘታቸዉ ታዉቋል። የተለያዩ ሃገራት ፖለቲካኞች እና የፖለቲካ ጉዳይ ምሁራን በሙኒኩ ጉባኤ ላይ አዉሮጳ በዓለም ፖለቲካ ያላት ተፅኖ ፈጣሪነት እየቀነሰ መምጣቱ ላይ ዉይይት አካሂደዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማርኮ አንድ ትልቅ ታኅድሶ እንደሚደረግ ይናገሩ እንጂ በዉል ምን አይነት የተሃድሶ ለዉጥ እንደሚደረግ በዉል አልገለፁም። 

 

ፀሐይ ጫኔ 

አዜብ ታደሰ