1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን

ሰኞ፣ ሰኔ 13 2014

የዓለም የስደተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታሰብበት በዛሬው ዕለት ፈረንሳይ ውስጥ ደግሞ የስደተኞች የምግብ ዝግጅት በአል በሚል በልዩ ዝግጅት እየተከበረ ነው።

https://p.dw.com/p/4CxOx
Frankreich Haitham Karajay Flüchtling aus Syrien Teilnehmer am Refugee Essenfest in Paris
ምስል Haimanot Tiruneh/DW

የስደተኞች የምግብ ዝግጅት በአል

የዓለም የስደተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚታሰብበት በዛሬው ዕለት ፈረንሳይ ውስጥ ደግሞ የስደተኞች የምግብ ዝግጅት በአል በሚል በልዩ ዝግጅት እየተከበረ ነው። በአሉ በስደተኛ ምግብ አብሳዮች እና በአካባቢው የምግብ ቤቶች መካከል ትብብርን ለመፍጠር በበጎ ፈቃደኛ ዜጎች ተነሳሽነት ከጎርጎሪዮሳዊው 2016 ዓም ጀምሮ በየዓመቱ የሚካሄድ ነው። በዚህ ዝግጅት ላይ የሚካፈሉ ኑሯቸውን በፈረንሳይ ያደረጉ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ስደተኞችን ጨምሮ ምግብ ማብሰል ፍላጎት ያላቸው እና በሙያው ለመሰማራት ለሚፈልጉ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ነገሮችን ለማመቻቸት ብሎም ከማኅበረሰቡ ጋር በቀላሉ ለመዋሃድ እንዲችሉ ይኽ በአል አስተዋጽኦ እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ