1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀገር ስጋት 

እሑድ፣ ጳጉሜን 3 2011

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አደጋ ላይ ነች የሚሉ ማሳሰቢያዎች መሰማት ከጀመሩ ውለው አደሩ። ይህን የሚሉት ወገኖች የተለያዩ መንስኤዎችን በማንሳት ነው ሀገር አደጋ ላይ ናት የሚሉበትን ስጋት ለማሳየት የሚሞክሩት።

https://p.dw.com/p/3PDnO
20.06.2013 DW Online Karten Basis Aethiopien spanisch

ውይይት

 ለአንዳንዶቹ  ሕገ መንግሥቱ  የአደጋ ምንጭ ነው፤  ለሌሎቹ ደግሞ ይኸው ሕገ መንግሥት ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች የሕልውና መሠረት ነው። ሕገ መንግሥቱ ከተነካም ለአደጋው ምንጭ ሊሆን እንደሚችልም ያሳስባሉ።  ከሰሞኑ ሕገ መንግሥቱ እና ፌደራላዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለማዳን በሚል መቀሌ ላይ የሁለት ቀናት ሀገር አቀፍ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር። ራሱ ያላከበረውን ሕገ መንግሥት ከአደጋ ለማዳን ጥሪ በማቅረብ ሀገሪቱን ላለፉት 27 ዓመታት የመራው ግንባር ተጠያቂ የሚያደርጉም አሉ። በእርግጥ ሕገ መንግሥቱ እና ፌደራል ሥርዓቱ አደጋ ላይ ነው? ዶቼ ቬለ ባካሄደው ውይይት ላይ  ለዚህ ስጋት መንስኤ የሆኑት ማመላከቻዎች እና ከአደጋ እናድነው የሚለውን ጥሪ የተቹ ወገኖች ተሳትፈዋል።

ሙሉ ውይይቱን ከድምፅ ማዕቀፉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ