1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦በለውጡ ሒደት የመገናኛ ብዙኃን ሚና

ቅዳሜ፣ ኅዳር 8 2011

ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ወራት ግድም ፈጣን ለውጦችን እያስተናገደች ነው። በለውጡ ሒደት በተለይ የመንግሥት የመገናኛ አውታሮች ተግባራቸውን እንዴት እየተወጡ ነው?   ለአንድ ወገን ብቻ በተለይ ለመንግሥት ወግኖ የመዘገብ ኹኔታቸውስ ምን ይመስላል? መገናኛ ብዙኃን በነጻነት እና በገለልተኝነት እንዲዘግቡ ምን ቢደረግ ይበጃል?

https://p.dw.com/p/38qf1
Karte Äthiopien englisch

ለመንግሥት ወግኖ የመዘገብ ኹኔታቸውስ ምን ይመስላል?

መገናኛ ዘዴ ካለው ብርቱ ተጽዕኖ የተነሳ የዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን በሚከተሉ ሃገራት ዘንድ የዲሞክራሲ አራተኛው ምሰሶ ተብሎ ይጠራል።  ከሕግ አውጪው፣ ከሕግ ተርጓሚው እና ከሕግ አስፈጻሚው እኩል መገናኛ ብዙኃን ለዲሞክራሲያዊ ሒደት ወሳኝ ተደርጎም ይወሰዳል። ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ወራት ግድም ፈጣን ለውጦችን እያስተናገደች ነው። በለውጡ ሒደት በተለይ የመንግሥት የመገናኛ አውታሮች ተግባራቸውን እንዴት እየተወጡ ነው? ለአንድ ወገን ብቻ በተለይ ለመንግሥት ወግኖ የመዘገብ ኹኔታቸውስ ምን ይመስላል? የመገናኛ አውታሮቹ በኹሉም መስክ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲጎለበት ጥረት እንደሚያደርግ በሚገልጠው በአዲሱ አስተዳደር ተግባራቸው በቀደመው አስተዳደር ከነበረው ምን ለውጥ አምጥቷል? መገናኛ ብዙኃን በነጻነት እና በገለልተኝነት እንዲዘግቡ ምን ቢደረግ ይበጃል? በውይይቱ ከተነሱ ዐበይት ጥያቄዎች መካከል ይገኙበታል። «በለውጡ ሒደት የመገናኛ ብዙኃን ሚና በኢትዮጵያ» በዚህ ሳምንት የሚቀርበው የውይይት መድረክ ዝግጅታችን ርእስ ነው። በዉይይቱ ከተነሱት ሐሳቦች ጥቂቱን እናሰማችሁ። 
                                              
ማንተጋፍቶት ስለሺ

ተስፋለም ወልደየስ