1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዋግ ኽምራ አፋጣኝ የምግብ ርዳታ ያሻዋል

ሐሙስ፣ ጥቅምት 6 2012

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ አስተዳደር ዞን ከ126 ሺህ በላይ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንደሚያስፈልገው ተገለጠ። ባለፈው ዓመት በነበረው ዝቅተኛ ዝናብ የተነሳ ከዞኑ ነዋሪዎች ገሚሱ አስቸኳይ ርዳታ የሚያሻው ነው ተብሏል።  አርሶ አደሮች አፋጣኝ መፍትኄ እንዲሰጣቸው ተማጽነዋል።

https://p.dw.com/p/3RT1X
Trockenheit im Westnordlische Äthiopien Waghmera Zone
ምስል DW/A. Mekonnen

አስቸኳይ ርዳታ በፍጥነት ሊደርስ ይገባል ተባለ

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ዞን ባለፈው ዓመት በነበረው ዝቅተኛ ዝንብ ምክንያት በተፈጠረው ድርቅ ምክንት በዞኑ ከሚገኙ አጠቃላይ 300 ሺህ  ነዋሪዎች መካከል 126 ሺህ ያህሉ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ መጋለጡን ከ60ሺህ በላይ እንስሳት ደግሞ በከፍተኛ የምግብ እጦት ላይ  መሆናቸውን የብሔረሰብ አስተዳደሩ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ደስታ ለዶይቼ ቬለ በስልክ አመልክተው እስካሁንም ምንም ዓይነት እርዳታ ወደ አካባቢው አልደረሰም ብለዋል፡፡

የችግሩን መነሻ ባለፈው ዓመት በአካባቢው በቂ ዝናብ በለመኖሩ ድርቅ በመከሰቱ እንደሆነ አቶ መልካሙ አብራርተዋል፡፡ እንስሳቱን ከርሀብ ለመታደግ ፍሬ አልባ የሆኑ ሰብሎች አገዳ አንዲሰበሰብ በማድረግ፣ አንዲሁም የተሸለ የእንስሳት መኖ ወደ አላቸው አካባቢዎች በማዘዋወር ምግብ የሚገኙበት ሁኔታ መቻቻል ብለዋል፡፡ 

አንድ የዝቋላ ወረዳ አርሶአደር በበኩላቸው ችግሩ አሳሳቢና አፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ ነው ነው ያሉት፡፡ የምግብ እርዳታው በፍጥነት ወደ አካባቢው ካልደረሰ ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚፈጠር አቶ መልክሙ ስጋታቸውን አስቀምተዋል፡፡

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ፣ የቅድሚያ ማስተንቀቂያና ምላሽ ዳሬክተር አቶ ጀምበሬ ደሴ በበኩላቸው ለ126 ሺህ ርዳታ ፈላጊ የኅብረተሰብ ክፍል አስቸኳይ የአንድ ወር የእለት የምግብ እርዳታ በቅርቡ ወደቦታው ይደርሳል ብለዋል፡፡ የዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር ዝናብ አጠር ከሆኑ የአማራ ክልል አካባቢዎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ