1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዋሽንግተን፤ ዶናልድ ትራምፕ 45ኛዉ የአሜሪካን ፕሬዝደንት ሆኑ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 30 2009

በዩናይትድ ስቴትስ የምርጫ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ተብሎ ሲተችና ሲብጠለጠል በቆየዉ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማን የሚተካ ፕሬዝደንት ለመምረት በተካሄደዉ ምርጫ የሪፐብሊካኑ እጩ ዶናልድ ትራምፕ 45ኛዉ ፕሬዝደንት መሆናቸዉን አረጋገጡ።

https://p.dw.com/p/2SOZz
US-Präsidentschaftswahl 2016 - Sieg & Rede Donald Trump
ምስል Getty Images/C. Somodevilla

 ከሀገሪቱ የሚወጡ ዘገባዎች የሚያመለክቱት የትራምፕ ድል ለተፎካካሪያቸዉ ዴሞክራቷ ሂላሪ ክሊንተን ብቻ ሳይሆን ለአብዛኛዉ አሜሪካዊ አስደንጋጭ እንደሆነ ነዉ። ትራምፕ በሀገሪቱ በሚካሄዱ ምርጫዎች ወሳኝ የሚባሉት ድምፆች የሚገኙባቸዉን ቁልፍ ግዛቶች በአብዛኛዉ ጠርገዉ ወስደዋል። በምርጫ ቅስቀሳቸዉ ወቅት አፋቸዉ እንዳመጣላቸዉ በመናገራቸዉ ብዙዎችን ሲያስደነግጡና ሲያበሳጩ የቆዩት ዶናልድ ትራምፕ ድላቸዉን ባበሰሩበት የመጀመሪያ ንግግራቸዉ አሜሪካዉያንን ወደ አንድነት ጋብዘዋል። ድላቸዉን እንዳረጋገጡ የመጀመሪያዉን የስልክ ጥሪ ከቶፎካካሪያቸዉ ከሂላሪ ክሊንተን እንደተቀበሉ የገለጡት ትራምፕ፤ እንኳን ደስያልዎት ያሏቸዉ ክሊንተንን ጠንካራ ተፎካካሪያቸዉ እንደነበሩ ሳይገልጹ አላለፉም። የዶናልድ ትራምፕ ቀጣሉ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንትነት ከተረጋፈጠ በኋላም፤ የተለያዩ ሃገራት አስተያየታቸዉን መሰንዘር ጀምረዋል። ቱርክ ከዋሽንግተን ጋር የጠበቀ ግንኙነት የምታደርግበት ጊዜ መድረሱን ስትናገር፤ ሩሲያ በበኩሏ ከእንኳን ደስ ያልዎት መልዕክቷ ጎን ለጎን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያላት ግንኙነት ይሻሻላል የሚል ተስፋ እንዳላት አመልክታለች።  ፈረንሳይ ትራምፕ የአሜሪካን ፕሬዝደንት መሆናቸዉ ከተረጋገጠ፤ ዋሽንግተን በሶርያ እና የኢራንን የኒኩለር ጉዳይ የተመለከተ ስምምነት እጣ ፈንታ ላይ ግልፅ ማብራሪያ እንደምትሻ ጠቁማለች። የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ፖሊስ የበላይ ፌዴሪካ ሞጎሪኒ፤ ኅብረቱ እና ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ መሥራታቸዉን እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።

ሸዋዬ ለገሠ