1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉይይት፣ ፍትሕ በረቀ ይሆን?

እሑድ፣ ኅዳር 9 2011

የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ መንግስት ሰባት ወር ሙሉ ሥለፍቅር፤ ይቅርታ፤ ሥለመቻቻል መደመር ሲሰብክ፣ ለማየት ዓይደለም ለመስማት የሚቀፈዉን ግፍ በይቅርታ ሰበብ የመጀቦኑ ዳርዳርታ መስሎ ብዙ አነጋግሮ፤አሳስቦ፤ ቅር አሰኝቶም ነበር።አዲሱ መንግሥት በሰባት ወሩ ጥርስ-ጥፍር አወጣ ያሰኝ ይሆን? ወይም ፍትሕ በረቀ።

https://p.dw.com/p/38Pjf
Waage der Göttin Justitia
ምስል picture-alliance/dpa

ዉይይት፣ ፍትሕ በረቀ ይሆን?

ተበዳይ፤ጉዳተኞች፤ ዘመድ-ወዳጆቻቸዉም በየጊዜዉ ጮኸዉበታል።በየፍርድ ቤቱ ተናግራዉታል።ጋዜጠኞች በየአጋጣሚዉ ዘግበዉታል።የመብት ተሟጋቾች አጋልጠዉታል።የሕግ ባለሙያዎች በየችሎቱ ተሟግተዉበታል።27 ዘመን።መንግሥት በቀደም በዳዮችን መክሰስ-ማሰሩን አረጋገጠ።የኢትዮጵያዉያንን የትዕግሥት ገደብ-ገደፉ ሞልቶ ከፈሰሰዉ ግፍ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ፀጋዬ ጥቂቱን ዘረዘሩ፤ ተጠርጣሪዎች ታሰሩም።

የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ መንግስት ሰባት ወር ሙሉ ሥለፍቅር፤ ይቅርታ፤ ሥለመቻቻል መደመር ሲሰብክ፣ ለማየት ዓይደለም ለመስማት የሚቀፈዉን ግፍ በይቅርታ ሰበብ የመጀቦኑ ዳርዳርታ መስሎ ብዙ አነጋግሮ፤አሳስቦ፤ ቅር አሰኝቶም ነበር።አዲሱ መንግሥት በሰባት ወሩ ጥርስ-ጥፍር አወጣ ያሰኝ ይሆን? ወይም ፍትሕ በረቀ።የዛሬ ዉይይታችን  ትኩረት ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ