1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ብሄራዊ (አገራዊ) ምክክር ብያኔዉ፣ሒደቱና ቅሬታዉ

እሑድ፣ የካቲት 20 2014

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የገዢዉ ፓርቲ ይሁኑ ተቃዋሚዎች፣ አማፂያን ይባሉ ሌላ፣ የፖለቲካ አቀንቃኝና ተንታኞችም ብሔራዊ ምክክር መደረጉን ይደግፋሉ።ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስትን በነፍጥ የሚወጉ ኃይላት፣ሰላማዊ ተቃዋሚዎችም ሆኑ የፖለቲካ አቀንቃኞች እስካሁን ያለዉን ሒደት አይቀበሉትም።

https://p.dw.com/p/47cuq
Äthiopien | National Dialogue
ምስል Yohannes Geberegziabher/DW

ዉይይት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ጅምር ጉዞ

ኢትዮጵያ በርስበርስ ጦርነት፣ በፖለቲካ ዉዝግብ፣ በድርቅና የምጣኔ ሐብት ድቀት መሐል ብሔራዊ ምክክር (National Dialogue) ለማድረግ ዝግጅቷን አገባድዳለች።የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ምክክሩን የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮችን በያዝነዉ ሳምንት መርጧል ወይም ሾሟል።ምክር ቤቱ እንዳስታወቀዉ 11ዱ ሰዎች የተመረጡት ሕዝብ ለኮሚሽነርነት ከጠቆማቸዉ ከ600 በላይ ዕጩዎች በየደረጃዉ ተጣርቶ ነዉ።

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች የገዢዉ ፓርቲ ይሁኑ ተቃዋሚዎች፣ አማፂያን ይባሉ ሌላ፣ የፖለቲካ አቀንቃኝና ተንታኞችም ብሔራዊ ምክክር መደረጉን ይደግፋሉ።ይሁንና የኢትዮጵያ መንግስትን በነፍጥ የሚወጉ ኃይላት፣ሰላማዊ ተቃዋሚዎችም ሆኑ የፖለቲካ አቀንቃኞች እስካሁን ያለዉን ሒደት አይቀበሉትም።

ገሚሶቹ ፖለቲከኞች ወይም የፖለቲካ ፓርቲዎች አጠቃላይ ሒደቱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅን ጨምሮ በሌሎች ገለልተኛ ወገኖች መመራት አለበት ሲሉ፣ ሌሎች ደግሞ በተለይ የኮሚሽነሮቹ ምርጫ ገዢዉ ፓርቲ በሚመራዉ ምክር ቤት መሆን አልነበረበትም ይላሉ።

Äthiopien Parlament Addis Abeba
ምስል Solomon Muche/DW

 

ኢትዮጵያ የገባችበት ጦርነት ሁነኛ መፍትሔ ሳይበጅለት ብሔራዊ ምክክር ማድረግ አይቻልም ባዮችም አሉ።የብሔራዊ ምክክር ብያኔ፣ ፅንሰ ሐሳቡ እና ዓላማዉ ራሱ በግልፅ አልተብራራም የሚል ቅሬታም ይሰማል።በዛሬዉ ዉይይታችን የብሔራዊ ምክክሩን ምንነት፣ የእስካሁን ሒደትና ቅሬታዉን እንቃኛለን።ሶስት እንግዶች አሉን።

1አቶ ባይሳ ዋቅወያ------የሕግ ባለሙያና የቀድሞ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት

2.አቶ አመሐ መኮንን-------የሕግ ባለሙያ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች

3. አቶ አቶ መኮንን ደያሞ-----የኢትዮጵያ ሕልዉና አድን ሕብረት ሊቀመንበር ናቸዉ

ነጋሽ መሐመድ