1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራት ህብረት

ዓርብ፣ ሐምሌ 28 2015

በአሶሳ ከተማ እና ባምባሲ ወረዳ በርካታ ወጣቶች ድርጅቱ ባደረገው ጥረት ከሱስ በመላቀቅ በራሳቸው ስራ እንዲሰማሩ ማድረግ መቻሉንም አብራርተዋል፡፡ በዚህን 2015 ዓ.ም ደግሞ ከመንዲ አምስት ወጣቶች በድርጅቱ ድጋፍ ከሱስ በማገገም ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4UnIu
Äthiopien | Assosa
ምስል Negassa Desalegn /DW

ወጣቶችን ከሱስ ያላቀቀው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራት ህብረት

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራት ህብረት (ቢ.ጂ፣ዳን) የተባለ የግል ድርጅት 160 የሚደርሱ ሰዎችን ከሱስ እና ከተለያዩ አልባለ ጎጂ ነገሮች ወደ መደበኛ ህይወታቸው እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ በማህበረሰብ አገልግሎት ስራ ለውጥ ማስመዝገቡን  የድርጅቱ ዋና ዳይረክተር አቶ ፋንታሁን መለሰ አመልክተዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ፣ ባምባሲ ወረዳ እና በምዕራብ ወለጋ ዞን ማናስቡ የተባለ ወረዳ ውስጥ እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ ከመንዲ ሆስፒታልና አሶሳ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ህክምና ተደርጎላቸው አብዛኞቹ ወጣቶች ከሱስ በመላቀቅ በግል ስራ መሰማራታቸውን አስረድተዋል።

በ2003 ዓ.ም የተመሰረተው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራት ህብረት በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሲሆን የአካባቢ ጥበቃ፣በሰላም እና ጤና ጉዳዮች  ላይ እንደሚሰራ ተገልጸዋል፡፡ ድርጅቱ ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ በሱስ እና  የተለያዩ ጎጅ ባህላዊ ድርጊቶች የተጎዱ ሰዎችን ከጤና ተቋማት ጋር በመቀናጀት በማስተማር፣በማሳከም ልዩ ልዩ ድጋፎችም ሲያደርግ መቆየቱን የድርጅቱ ዳይረክተር አቶ ፋንታሁን መለሰ ተናግረዋል፡፡ 

በአሶሳ ከተማ እና ባምባሲ ወረዳ በርካታ ወጣቶች ድርጅቱ ባደረገው ጥረት ከሱስ በመላቀቅ በራሳቸው ስራ እንዲሰማሩ ማድረግ መቻሉንም አብራርተዋል፡፡ በዚህን 2015 ዓ.ም ደግሞ ከመንዲ አምስት ወጣቶች በድርጅቱ ድጋፍ ከሱስ በማገገም ወደ መደበኛ ህይወታቸው መመለሳቸውን ገልጸዋል፡፡ ህክሚናና ድጋፍ ከተደረገላቸው በኃላ ተመልሰው ወደ ሱስ የሚመለሱት ወጣቶችም መኖራቸውን የገለጹት ኀላፊ  በሱስ የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን መንከባከብና ለመጠበቅ የሁሉም ተቋማት ጥረት ይጠይቃል ብሏል፡፡ ሱስ ሀገር ተረካቢ ትውልድን የሚያቀጭጭ በሽታ በመሆኑ ከጤና ተቋማት በኩል ልዩ ድጋፍ እና  ትኩረት እንደሚያስልገው ተናግረዋል፡፡ 

አቶ ጌታሁን በ2009 ዓ.ም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራት ህብረት  በኩል ህክምና ሲደርግለት እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ለወራት ህክምና ከተደረገለት በኃላ በአሁኑ ጊዜም በግል ስራ ላይ ተሰማርተው እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ ከጓደኞቻቸ ጋር በመሆን 1ሺ ካሬ መሬት ላይ የብሎኬትና የእንጨት ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ 
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራት ህብረት (ቢ.ጂ፣ዳን) ከተለያዩ የግል ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚሰራ ሲሆን ሱስና መጤ ባህሎች ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር እና የመከላከል  ተልዕኩን አንግቦ እንደሚቀሳቀስ ተገልጸዋል፡፡ ብሪቲሽ ካውንስልና ፓክት የተባሉ ተቋማት ለድርጅቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማት መሆናቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ልማት ማህበራት ህብረት  ኃላፊ አቶ ፋንታሁን መለሰ ተናግረዋል፡፡   
ነጋሳ ደሳለኝ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ