ወደባንክነት ያደገው የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም
ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2012ማስታወቂያ
አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) ወደ ባንክነት ማደግ የሚያስችለውን ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ። በሦስት ሚሊዮን ብር ካፒታል በ1988 ዓ.ም ሥራውን የጀመረው ይህ ተቋም ዛሬ አጠቃላይ ሀብቱን 36 ቢሊዮን ብር ማድረስ ችሏል። ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ የብድር እና ቁጠባ ደንበኞች እንዳሉትም ታውቋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የተቋሙ ደንበኞች በተቋሙ የፋይናንስ አገልግሎት መለወጥ መቻላቸውን ይገልጻሉ። ከባሕር ዳር ዓለምነው መኮንን ዝርዝር ዘገባ አለው።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ