1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወልድያ እንዴት ሰነበተች?

ዓርብ፣ ሐምሌ 23 2013

አንድ የወልዲያ ከተማ ነዋሪም እንዳረጋገጡልን የሀሰት ወሬ ባናፈሱ ሰዎች ከአንድ ቀን በፊት በወልዲያ ከተማ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰው ወሬው መሰረት የሌለው እንደነበርና ህብረተሰቡ አሁን በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። 

https://p.dw.com/p/3yKnP
Tigray-Konflikt | Militär in Addis Abeba
ምስል Minasse W. Hailu/AA/picture alliance

ወልድያ እንዴት ሰነበተች?

ካለፉት ጥቂት ሳምንታት ጀምሮ የህወሓት ኃይሎች በሰሜንና ምዕራብ አማራ አንዳንድ አካባቢዎች ወረራ በመፈፀም የአካባቢውን ነዋሪዎች ማንገላታታቸውን፣ ዘረፋና ሌሎች ያልተገቡ ተግባራት መፈፀማቸውን የአማራ ክልል መንግስት በተደጋጋሚ አስታውቋል።

ህወሓት በአላማጣንና በቆቦ በቅርቡ ጥቃት በመፈጠሙ በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች ተፈናቅለው ወደ ወልዲያ ከተማ ገብተዋል።ከተፈናቃዮች መካከል አንዱን አነጋግረናቸው ነበር። ወልዲያ በህወሓት ኃይሎች ተይዛለች እየተባለ የሚናፈሰው የሽብር ወሬ ፍፁም ሀሰትና ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የሚያስወሩት ወሬ ነው ብለዋል፣ በወልዲያ ህዝብ ድጋፍ በአንድ ትምህት ቤት እንደተጠለሉም አብራርተዋል። 

ሌላው ጉዳዩን በቅርበት ከወልዲያ የሚከታተለው የራያ ቆቦ ተፈናቃይ እንደገለፀልን ደግሞ ከቆቦ የተፈናቀሉ ወጣቶች በጠየቁት መሰረት እየተደራጁ አካባቢያቸውን እየጠበቁ ነው፡፡ ሴቶችና ህፃናት ተፈናቃዮች ግን በወልዲያ ህዝብ እየታገዙ ወልዲያ ከተማ ውስጥ እንደሚኖሩ አመልክተዋል። አሁን ያለውን የወልዲያ ወቅታዊ ሁኔታ ሰላማዊ እንደሆነም አስረድተዋል።

አንድ የወልዲያ ከተማ ነዋሪም እንዳረጋገጡልን የሀሰት ወሬ ባናፈሱ ሰዎች ከአንድ ቀን በፊት በወልዲያ ከተማ አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰው ወሬው መሰረት የሌለው እንደነበርና ህብረተሰቡ አሁን በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል። 

የተፈናቃዮችን አያያዝና በአካባቢው ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከመንግስት አካል አስተያየት ለማካተት ያደረግሁት ጥረት አልተሳካም።
ዓለምነው መኮንን
ሸዋዬ ለገሰ