1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ወልቂጤን ጨምሮ በጉራጌ ዞን ከተሞች የሥራ ማቆም አድማ

ሰኞ፣ ጥር 29 2015

በስድስቱ ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ለሕዝበ ውሳኔ ድምጽ ሲሰጥ። በዚያው በደቡብ ክልል የሚገኘው የጉራጌ ዞን ከተሞች በአንጻሩ የሥራ ማቆም አድማ ተደርጓል።ለአራተኛ ግዜ የሚደረገውን አድማ አስተባብራችዋል ቅስቀሳ አድርጋችዋል የተባሉ ወጣቶች በመንግስት አካላት ድብደባ እና እስራት እየደረሰባቸው ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4N9nY
Äthiopien Gurage Streik
የተዘጉ ሱቆች በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ምስል privat

ለአንድ ቀን የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን

በደቡብ ክልል በሚገኘው ጉራጌ ዞን ዋና ከተማ ወልቂጤን  ጨምሮ በተለያዩ  አካባቢዎች በዛሬው እለት ለአንድ ቀን የሚቆይ የስራ ማቆምና ከቤት ያለመውጣት አድማ እየተደረገ መሆኑን  ዶቼ ቬሌ ያነጋገራቸው የዞኑ ነዋሪዎች ተናገሩ።

ዛሬ ማለዳ የጀመረው የስራ ማቆም አድማ ለአንድ ቀን ብቻ እንደሚቆይ የተናገሩት የአድማው አስተባባሪ እና የወልቂጤ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ አንድነት አንዱሎ የአድማው የተደረገበትን ምክንያት ዛሬ በደቡብ ክልል የሚከናወነው ህዝበ ውሳኔ ዛሬ ወደ ወላይታ ጋሞ ምርጫ እያደረጉ ነው ጉራጌ ግን በሙሉ ድምፁ ያፀደቀው እና በምክር ቤቱ የወሰነው ውሳኔ በግድና በጉልበት ማእከላዊ ኢትዮጵያ ተብለህ ተሰየም  በመባላችን ነው ይላሉ ። «ህዝቡ ተቃውሞውን በሰላማዊ መንገድ ቤት ውስጥ በመቀመጥ  አድማ እያደረገ ነው» ብለዋል።

ለአራተኛ ግዜ የሚደረገውን የስራ ማቆም እና ቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማን አስተባብራችዋል ቅስቀሳ አድርጋችዋል የተባሉ ወጣቶች በመንግስት አካላት ድብደባ እና  እስራት እየደረሰብን  ያሉት አቶ  አንድነት

«ህዝቡን ስለመብቱ ሲያነቁ እና ሲያስተባብሩ የነበሩ ወጣቶችን ትላንት የመንንግስት አካላት  አስረዋቸዋል። መንግስት  አሁን ላይ ምላሽ እየሰጠን ያለው በእስራት ነው ብለዋል

ሌላኛው ለዶቼ ቬሌ አስተያየታቸውን የሰጡት የጉራጌ ዞን ነዋሪ የሆኑት ሰንብት መስሩ እሳቸው ባሉበት አካባቢ ከጤና ተቋም በስተቀር ሁሉም ዝግ እንደሆኑ ተናግረዋል። ማህበረሰቡ ጋር ተቀባይነት ያላቸውን እንዲሁም ማህበረሰቡን የሚያነቁ ሰዎች በተለይ ወጣቶች ከትላንት ጀምሮ በመንግስት የፀጥታ አካላት እየታሰሩ እንደሆነ ና እሳቸው በሚኖሩበት አካባቢ ከጤና ተቋም ውጪ ሁሉም ነገር ዝግ መሆኑን ተናግረዋል «የመንግስት የፀጥታ አካላት  ዛቻና ማስፈራሪያ ከማድረግ ውጪ እስራት እየፈፀመ ነው» ብለዋል  

ከዚህ በፊት በጉራጌ ዞን የሚገኙ አምስት የወረዳ ምክር ቤቶች አሁን ያለውን የደቡብ ክልል ለሁለት የሚከፍለው የክላስተር አደረጃጀት «ገቢራዊ ይሁንልን» ሲሉ ለአገሪቱ የፌዴሬሽን ም/ቤት መጠየቃቸው ይታወሳል።

ለጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን ኃላፊዎች  ለአንድ ቀን በሚቆየው የሥራ ማቆም አድማ እና ታሰሩ ስለተባሉት  የማህበረሰቡ ክፍሎች ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ሀሳባቸውን ልናካትት አልቻልንም።

Äthiopien Gurage Streik
የተዘጉ የንግድ ቤቶች በደቡብ ክልል በሚገኘው ጉራጌ ዞን ምስል privat

ትላንት  ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም የጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በሰጠዉ መግለጫ «ጥር 29 ህዝበ ዉሳኔ ከእኛ ዞን ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም» ብሎ ነበር። 

የዞኑ የኮሙኒኬሽን መምሪያ በማኅበራዊ ድረ ገጾች ባሰራጨው መግለጫ «ቀኑን ክልል ወይም ዞን እንዲሁም ልዩ ወረዳ  የሚመሰረትበት ቀን በማስመሰል ፀረ ሰላም ሀይሎች አመፅ ለመቀስቀስ በማህበራዊ ሚዲያ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛል» በማለት በስም ያልጠቀሳቸውን ወገኖች ከሷል። 

«የዞኑን ህዝብ ሰላም ለማደፍረስ፣የመማር ማስተማር ሂደትን ለማስተጓጎል፣ ህዝቡ የዕለት ኑሮዎን ለማሸነፍ የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ለማደናቀፍ» ይሞክራሉ ላላቸው አካላት «ነውጠኛ» ካለው ተግባር እንዲታቀቡ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።

የዞኑ አስተዳደር «የህዝብን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ህገወጥ ቡድኖች ላይ መንግስት ጠንካራ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ በቂ ዝግጅት» ማድረጉንም የጉራጌ ዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ገልጿል።

ማህሌት ፋሲል

እሸቴ በቀለ