1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 ኮቪድ 19 እና የክትባት ምርምር

ማክሰኞ፣ የካቲት 16 2013

ዓለምን ካዳረሰ ዓመት ያለፈው ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ብቻ የገደላቸው 500 ሺህ ደርሰዋል። በመላው ዓለም የሟቾች ቁጥር ከ2,4 ሚሊየን አልፏል። እስካሁን በበሽታው የተያዙት ደግሞ ከ111 ሚሊየን በላይ ናቸው። በዚህ መሀል ከህመሙ ያገገሙ 85 ሚሊየን ገደማ እንደሆኑም መረጃዎች ያሳያሉ።

https://p.dw.com/p/3pkuv
Libanon Beirut | Coronaimpfung
ምስል Marwan Naamani/dpa/picture alliance

ኮቪድ 19 እና የክትባት ምርምር

እናም አሁን ዓለም ትኩረቱን ክትባቱ ላይ አድርጓል። ካለፈው ታኅሣስ ወር አንስቶ የተለያዩ ሃገራት የኮቪድ 19 ክትባትን ይበልጥ ተጋላጭ ለሚሏቸው ለዜጎቻቸው መከተብ ጀምረዋል። በአውሮጳ ቀዳሚዋ ብሪታንያ ስትሆን እስካሁን የእስራኤል ያህል ክትባቱን ለዜጎቹ ያዳረሰ የለም እየተባለ ነው።  በኤኮኖሚ የጠነከሩት ሃገራት የተሻሉ ያሏቸውን የምርምር ውጤቶች ለዜጎቻቸው ለማዳረስ እየታገሉ ቢሆንም የተጠበቀውን ያህል የክትባት ምርቱ ገና አልተዳረሰም። ክትባቶች በረዥም ዓመታት ሙከራ ውጤታማነታቸው እንደሚጠና እና ፈቃድ እንደሚሰጣቸው ባለሙያዎች ይናገራሉ።  የኮቪድ 19 ክትባት ግን በወራት ውስጥ መድረሱ እንዴት? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱ አልቀረም። ባለፈው ሳምንት ስለተሐዋሲን በተለይም ስለኮቪድ 19 ለሚነሱ ጥያቄዎች በጀርመን ሀገር ላይፕዚሽ ከተማ ሄሊዮን ክሊኒክ የውስጥ ህክምናና በተሐዋሲያን የሚመጡ በሽታዎች ህክምና ዘርፍ ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ስንታየሁ አሰፋ ሰፋ ያለ ማብራሪያ እንደሰጡን ይታወሳል። ከዶክተር ስንታየሁ ጋር ባደረግነው ቃለ መጠይቅም የኮሮና ክትባትን አስመልክቶ ብዙዎች የሚያነሱትን ጥያቄ እኛም አንስተን ነበር። ከዶክተር ስንታየሁ አሰጋ ጋር ያደርግነው ቃለ መጠይቅ ክፍል ሁለት መልሱን አካቷል። ከድምፅ ማዕቀፉ ያድምጡ፤

ሸዋዬ ለገሠ 

ኂሩት መለሰ