ኮቪድ 19 ሁለተኛ ዙር ወረርሽኝ በአውሮጳ
ዓርብ፣ ጥቅምት 20 2013ማስታወቂያ
በአውሮጳ ዳግም በፍጥነት እየተስፋፋ የመጣው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ለመግታት የሕብረቱ አባል መንግሥታት ጥብቅ ርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ናቸው። የተሐዋሲው ስርጭት በየዕለቱ እየጨመረና እየተባባሰ መምጣቱ ሁሉንም የአውሮጳ ሃገራት አስጨንቋል። በዚህም ምክንያት የሕብረቱ መሪዎች ትናንት በዚሁ ጉዳይ ላይ የቪዲዮ ጉባኤ አካሂደዋል። ፈረንሳይና ጀርመንን ጨምሮ ብዙዎቹ አባል መንግሥታት መጠጥ ቤቶችና ምግብ ቤቶችን፤ የባህልና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፤ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዘጉ ወስነዋል። የሰዓት እላፊ አዋጅም ደንግገዋል። ገበያው ንጉሤ ከብራስልስ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ገበያው ንጉሤ
ሸዋዬ ለገሠ
ማንተጋፍቶት ስለሺ