1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኮሮና በድሬዳዋ

ማክሰኞ፣ ጥር 11 2013

በድሬደዋ አስተዳረደር ያለው የኮሮና ስርጭት በህብረተሰቡ ዘንድ በሚታየው መዘናጋትና ቸልተኝነት ላይ ተመስርቶ እየተባባሰ መሆኑን የተለያዩ አተያየት ሰጭዎች ገለፁ፡፡ በሆቴል አገልግሎት እና ትራንስፖርት ዘርፍ ላያ ያለው መዘናጋት ለዚህ በአብነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3o8Yp
Stadt Dire Dawa in Äthiopien
ምስል Hailegzi Mehari

መዘናጋቱ አሁንም አለ

በድሬደዋ አስተዳረደር ያለው የኮሮና ስርጭት በህብረተሰቡ ዘንድ በሚታየው መዘናጋትና ቸልተኝነት ላይ ተመስርቶ እየተባባሰ መሆኑን የተለያዩ አተያየት ሰጭዎች ገለፁ፡፡ በሆቴል አገልግሎት እና ትራንስፖርት ዘርፍ ላያ ያለው መዘናጋት ለዚህ በአብነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በድሬደዋ አስዳደር ትራፊክ ዘርፍ እየሰሩ ያሉት ኢንስፔክተር ጌትነት ችግሩ መባባሱን ተከትሎ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ለአሽከርካሪዎች ግንዛቤ መሰጠቱን ጠቅሰው በቀጣይ በህግ የተቀመጠው አሰራር ለመተግበር እንቅወቃሴ ይደረጋል ብለዋል። 

የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ በበኩላቸው በመስተዳድርሩ እስካሁን በነበረው ጊዜ ሃያ ዘጠኝ ሰዎች ህይወት በኮሮና ሳቢያ ማለፉን ጠቅሰው መከላከል በሚቻል ችግር የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ህብረተሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

በድሬደዋ ቀደም ሲልም መዘናጋት ውስጥ የገባው ህብረተሰብ ከትናንት ጀምሮ እየተከበረ ባለው የጥምቀት በዓል ዝንጉነቱ ይበልጥ መባባሱን ለመታዘብ ችያለሁ፡፡ መስተዳድሩ ግን ከጥር ቀን ጀምሮ ምንም ዓይነት አገልግሎት ያለ ማስክ አጠቃቀም እንዳይከናወን የሚል ዘመቻን ይፋ አድርጓል። 

መሳይ ተክሉ

ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ