1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትንሳኤ በዓል ግብይት በመቐለ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 7 2015

በመቐለ የተለያዩ ገበያዎች ተዘዋውረን እንደተመለከትነው ደሮ እስከ 2 ሺህ ብር፣ በግና ፍየል በአማካኝ እስከ 15 ሺህ ብር፣ የበሬዎች ዋጋ እስከ 140 ሺህ ብር ሲሸጡ ውለዋል።

https://p.dw.com/p/4Q8a8
Äthiopien | Mekele Äthiopischer Ostermarkt
ምስል Million HaileSilasse/DW

የደሮ ዋጋ የድሮ የበግ ዋጋ ያህል ነው

የዘንድሮ የትንሳኤ ብዓል ዋዜማ ድባብ በመቐለ የደመቀ ሆንዋል። ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በሸቀጦች እና የእርድ ከብቶች ላይ ቢታይም ገበያዎች በሸማችና ሻጮች ተሞልተዋል፣ የከተማዋ እንቅስቃሴ ደርቷል፣ ከጦርነቱ በኃላ የተሻለ የሚባል የበዓል ድባብ ይታያል። በመቐለ የተለያዩ ገበያዎች ተዘዋውረን እንደተመለከትነው ደሮ እስከ 2 ሺህ ብር፣ በግና ፍየል በአማካኝ እስከ 15 ሺህ ብር፣ የበሬዎች ዋጋ እስከ 140 ሺህ ብር ሲሸጡ ውለዋል። ይህ ካለፈው ዓመት አልያም ያለፉ በዓላት ወቅት ሲነፃፀር እስከ 300% ጭማሪ ይታይበታል ተብሏል። በሁሉም ሸቀጦች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ቢኖርም በመቐለ የበዓሉ ድባብ ግን ካለፉት ግዚያት የተሻለ ሆንዋል።

ሚልዮን ሃይለስላሴ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር