1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኪምፓ ቪታ

Carla Fernandes
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 15 2012

በ 18ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የኮንጎ ሥርወ መንግሥት አንዲት ወጣት ነብይት ነኝ ባይ አስተናግዷል። ኪምፓ ቪታ የፖርቹጋልን የቅኝ ገዢዎች ለመዋጋት የመንግሥታቸውን ወታደሮች ያጠናከሩ የአንድነት ሰባኪ ተደርገው ይታወሳሉ።

https://p.dw.com/p/3bE6G
Projekt African Roots

ኪምፓ ቪታ መቼ ይኖሩ ነበር?
ኪምፓ ቪታ  እጎአ 1684 ዓ ም ገደማ በአሁኑ ጊዜ የአንጎላ ክልል ውስጥ በሚገኘው እና ኪባንጉ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደተወለዱ ይታመናል። ኪምፓ ቪታ ካልተሳኩ ሁለት ትዳሮች በኋላ ወደ መንፈሳዊ ሕይወት እንደተዛወሩ ይነገራል። በሌላ በኩል ደግሞ ገና ከልጅነታቸው እድሜ አንስቶ ራእዮች ነበሯቸው ይባላል።  

የኪምፓ ቪታ አስተዳደግ እንዴት ነበር?
ታዋቂ የሆነ ቤተሰብ የነበራቸው ኪምፓ ቪታ የሰለጠኑት «ናጋንጋ ማሪንዳ» ማለትም ከክፉ ፈዋሽ ሆነው እንዲያገለግሉ ነው። እሳቸውም በሕይወት እና በሞት መካከል ፣ ባሉ እና መሞት በተለዩ ቅድመ አያቶች መካከል አማላጅ ነበሩ። 

ኪምፓ ቪታ -- የኮንጎ ሥርወ መንግሥት የአንድነት ነብይት

ኪምፓ ቪታ የታወቁት በምንድን ነው?  አገልግሎት በሰጡበት አጭር እድሜ የኮንጎን ሥርወ መንግሥት አንድ የማድረግ አቅም አሳይተዋል። እርሳቸውም የአንቶንኒያን ንቅናቄ  መሥራች ሆነው ይታወሳሉ። 

የኪምፓ ቪታ ንቅናቄ ምንን አስመልክቶ ነበር?
የአንቶኒያኒዚም ንቅናቄ ሓይማኖታዊ ንቅናቄ ነበር። ኪምፓ ቪታ የክርስትና እምነትን ከአፍሪቃ ባህላዊ ሓይማኖታዊ አምልኮዎች ጋር ያዋህዱ ነበር። በመጨረሻው የህይወት ዘመናቸውም በፓዱዓ ቅዱስ አንቶኒ አማካኝነት ዳግም ወደዚች ምድር ተመልሰው እንደተላኩ ይናገሩ ነበር። እየሱስ ክርስቶስም ጥቁር መሆኑን እና ኮንጎ ውስጥ መወለዱን ይሰብኩ ነበር። ከዚህም ንቅናቄ በኋላ አፍሪቃ ውስጥ የተለያዩ ሓይማኖታዊ ንቅናቄዎች እንደ ኩዊባንዳ ፣ ቶኮኢስሞ የመሳሰሉ ንቅናቄዎች ተከናውነዋል። እጎአ በ1920 ዎቹ የተመሰረተው የኪምባንጉዊስት ቤተ ክርስትያንም የአንቶኒያኒዝም ንቅናቄ ውጤት ተደርጎ ይታያል። 

Projekt African Roots

ኪምፓ ቪታ እንዴት ሞቱ?
እጎአ 1706  ጠንቋይ እና መናፍቅ ናቸው በሚል ተቃጥለው እንዲሞቱ ተፈርዶባቸዋል። ተልኮው የመጣውም በቤርናንዶ ዳ ጋሎ ይመሩ በነበሩ መለኩሴዎች አማካኝነት ነው።

ስለ ኪምፓ ቪታ ምን አይነት ታሪኮች ይንሸራሸራሉ?
ከአንዱ አገልጋያቸው እንዳረገዙ እና የንጉስ ፔድሮ ወታደሮች ልጃቸውን እያጠቡ እንዳሉ እንደያዟቸው ይነገራል። እስካሁን ድረስ የኪምፓ ቪታ ልጅ እጣ ፈንታ ምን እንደሆነ አይታወቅም። ስለ ኪምፓ ቪታ ከተመዘገቡ እና ከሚታወቁ ነገሮች አንዱ ተቃጥለው እንዲሞቱ አንድ መለኩሴ እንደፈረዱባቸው ነው። እንደ መለኩሴው ከሆነ ደግሞ ልጃቸውን ምረውታል። በአፈ ታሪክ እንደሚባለው ከሆነ ደግሞ ልጃቸውም ከኪምፓ ቪታ ጋር 1706 አብሮ ተቀብሯል።  

ኪምፓ ቪታ

ይህ ዘገባ አፍሪካዊ ሥረ-መሠረት በሚል ከጌርዳ ሔንክል ተቋም ጋር በመተባበር የሚቀርብ ዝግጅት ነው። የዘገባው ሳይንሳዊ ምክር የተገኘው ከፕሮፌሰር ጉዳዬ ኮናቴ፣ ሊሊ ማፌላ Ph.D እና ፕሩፌሰር ክሪስቶፈር ኦግቦግቦ ነው።