1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሙዚቃ

ከጃኖ ባንድ አባላት ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ

እሑድ፣ ጥቅምት 11 2011

«በሥራው ዓለም ዋነኛው በልዩነት መግባባት መቻል ነው። ሁሉም የራሱ የሆነ ተፈጥሮ የለገሰችው ቅላጼና ችሎታ አለው። እንደ ሕብረ ቀለም በአንድ ሲዋሀድ ውበትን ያደምቃል። የአንዱ ክፍተት በአንዱ ይሞላል። የአንዱ ስህተት በአንዱ ይሸፈናል። ለዚህም በጥንድ መሆኑ እጅጉን አስተዋጽኦ አለው» የጃኖ ባንድ አባላት።

https://p.dw.com/p/36uk8
Jano Band | Musikband aus Äthiopien
ምስል Jano Band

መዝናኛ፦ከጃኖ ባንድ አባላት ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ

በቡድን ሆነው ሲዘፍኑ በማናይበት በዚህ ዘመን የሙዚቃው አለም ብቅ ያሉ ድምጸ መረዋዎች። ሲዘሉ ለተመለከታቸው ዘለው ያልጠገቡ ይላቸው ይሆናል። መድረኩ የማይበቃቸው እያዝናኑ የታዳሚዎቻቸውን ቀልብ መያዝ የሚችሉ ወጣቶች ድምጻዊያን። ጃኖ ባንድ። ጥቂት ሙዚቀኞች ጥንድ ሆነው ጀምረው ሳያዛልቃቸው ቀርቷል። 

«በሥራው አለም ዋነኛው በልዩነት መግባባት መቻል ነው። ሁሉም የራሱ የሆነ ተፈጥሮ የለገሰችው ቅላጼና ችሎታ አለው። እንደሕብረ ቀለም በአንድ ሲዋሀድ ውበትን ያደምቃል። የአንዱ ክፍተት በአንዱ ይሞላል። የአንዱ ስህተት በአንዱ ይሸፈናል። ለዚህም በጥንድ መሆኑ እጅጉን አስተዋጽኦ አለው» ይላሉ የጃኖ ባንድ አቀንቃኞች ዲበኩሉ ታፈሰ፣ ሃሌሉያ ተክለጻዲቅ፣ ሔዋን ገብረወልድ እና ኃይሉ አመርጋ። ስምንት ዓመታትን ሙዚቃን በጋራ ሰርተዋል። ኤርታሌ እና ለራስህ ነው የተሰኙ ሁለት አልበሞችንም አሳትመዋል። በቅርቡም «ጥቁር አልማዝ» የሚል ነጠላ ዜማ ለአድማጮቻቸው አቅርበዋል።

የተሻለ ስራ ለመስራትም ጥረት እንደሚያደርጉ ይገልጻሉ። የግል ፍላጎታቸውን እየተው በአንድነት እንደሚሰሩ መደጋገፉ እንዳለ ሆኖ ጥንካሬንና ትእግስትን ይጠይቃል። በህብረት መስራቱ ለውጥ ማምጣት በመቻሉ ረገድ እንደማያጠያይቅ ለ8 አመታት በቆይታቸው ለሙዚቃው አርአያነታቸውን እንዳሳዩ ይናገራሉ።

ሙሉው ዝግጅት ማገናኛው ላይ ይገኛል

ነጃት ኢብራሒም

ሸዋዬ ለገሰ