1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከበሽታው የተረፉትን መደገፍ

ዓርብ፣ የካቲት 13 2007

የኢቦላ ተዛማች በሽታን ተቋቁመው የተረፉ ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ መገለል እና አድልዎ ይገጥማቸዋል። ብዙዎቹ ከዚህ በሽታ የተረፉ ሰዎች ወዳጆቻቸው ከእነሱ ጋር ምንም ነገር ማድረግ እንደማይፈልጉ ይገነዘባሉ፤ አንዳንዶቹ እንደውም ሥራቸውን ሁሉ ያጣሉ። ይኽ ተገቢ አይደለም።

https://p.dw.com/p/1Ef5q
Liberia Ebola Überlebende
ምስል John Moore/Getty Images

የኢቦላ ኅመምተኛ የነበረ ሰው የበሽታው ምልክቶች ከሰውነቱ ላይ ከጠፉ ከጥቂት ቀናት በኋላ የበሽታው አስተላላፊነቱ ያከትማል፤ በእርግጥ ተሐዋሲው በዘር ፈሣሹ ውስጥ ለበርካታ ሣምንታት መቆየት መቻሉ መዘንጋት የለበትም። ስለዚህም ከኢቦላ በሽታ የተረፉ ሰዎች የኢቦላ ተሐዋሲ ምልክቶች ከሰውነታቸው ላይ ከጠፉበት ጊዜ አንስቶ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ኮንዶሞችን ሊጠቀሙ ይገባል።

ከኢቦላ በሽታ የተረፉ ሰዎች ደም በኢቦላ ተሐዋሲ ዳግም እንዳይጠቁ የሚያስችሉ የሰውነት በሽታ ተከላካዮችን የያዘ ነው። እነዚህ የበሽታ ተከላካዮች የኢቦላ ኅመምተኞችን ለመርዳት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።

ከኢቦላ በሽታ የተረፉ ሰዎችን መሸሽና እና ማግለል አያስፈልግም። ርዳታ ያሻቸዋል። እጅግ በጠና ኅመም ተሠቃይተዋል፤ ብዙዎቹ በተሐዋሲው የቤተሰብ አባላቸውን አጥተዋል። ኅብረተሰቡ በተቻለ መጠን ሊደግፋቸው እንጂ፥ ጭራሽ መከራቸውን ሊያባባስ አይገባም።