1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከቀረጥ ነጻ በሆኑ የኢንቬስትመንት ፈቃዶች የተፈፀሙ ወንጀሎች እና የኢትዮጵያ እርምጃ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 15 2011

የኢትዮጵያ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተለይ ከ DW ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አሁን የተጀመረውን አገራዊ ለውጥ ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ እና ህገወጥ ያሏቸውን ነጋዴዎችን እና ኮንትሮባንዲስቶችን ለህግ ለማቅረብ የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል::

https://p.dw.com/p/3Aayl
Äthiopien Ministerin für Finanzen Adanech Abebee
ምስል Ethiopian Ministry of Revenues

ከቀረጥ ነጻ በሆኑ የኢንቬስትመንት ፈቃዶች የተፈፀሙ ወንጀሎች እና የኢትዮጵያ እርምጃ

ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቀረጥ ነጻ ኢንቨስትመንት ስም ከ 400 ቢልዮን ብር በላይ ለልማት ሊውል ይችል የነበረ ገንዘብ ማጣቷ ተገለጸ። መሰረተ ልማት ለሌላቸው የጠረፋማ አካባቢ ነዋሪዎች የዕለት የምግብ ፍጆታ እና አልባሳት በተዘረጋው የፍራንኮ ቫሉታ የግብይት ሥርዓትም በ 3 ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ 14.3 ቢልዮን ብር በላይ ማጣቷን የፌደራል መንግስት የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቋል:: የኢትዮጵያ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በተለይ ከ DW ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አሁን የተጀመረውን አገራዊ ለውጥ ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ እና ህገወጥ ያሏቸውን ነጋዴዎችን እና ኮንትሮባንዲስቶችን ለህግ ለማቅረብ የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል:: ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል:: 
እንዳልካቸው ፈቃደ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ