1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሰቆጣ ዳግም የተፈናቀሉ ነዋሪዎችዋ ሮሮ 

ሰኞ፣ መስከረም 3 2014

ሰቆጣ ከተማ ነሐሴ 9/2013 ዓ ም በህወሓት ከተያዘች በኋላ ነሐሴ 27/2013 ዓ ም እንደገና በመንግስት ኃይሎች ቁጥጥር ስር ቆይታ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ጳጉሜን 5 ምሽት ዳግም በህወሃት ኃይሎች ስር እንደዋለች በዳህና ፣ በጭላና ቆዝባ የሚገኙ ተፈናቃዮች ተናግረዋል፤ህብረተሰቡ ለበዓሉ የገዛቸውን እንስሳት ሳያርድ በሌሊት መፈናቀሉን ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/40GkO
Äthiopien | Nefas Mewuch
ምስል Belete Tigabe

ከሰቆጣ ዳግም የተፈናቀሉ ነዋሪዎችዋ ሮሮ 


በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ለሁለተኛ ጊዜ የተፈናቀሉ የሰቆጣ ነዋሪዎች ለከፋ ርሀብ መገለጣቸውን አስተወቁ፡፡የሰቆጣ ከተማ ለሁለተኛ ጊዜ በህወሓት ስር ከወደቀች በኋላ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ጥለው ተሰድደዋል፤ መንግስት በበኩሉ ተፈናቃዮቹን ለመታደግ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡ሰቆጣ ከተማ ነሐሴ 9/2013 ዓ ም በህወሓት ስር ከቆየች በኋላ ነሐሴ 27/2013 ዓ ም እንደገና በመንግስት ኃይሎች ቁጥጥር ስር ቆይታ እንደገና በአዲስ ዓመት ዋዜማ ጳጉሜን 5 ምሽት በህወሃት ኃይሎች ስር እንደዋለች ከተፈናቃዮች መካከል በዳህና ፣ በጭላና ቆዝባ የሚገኙ ተፈናቃዮች ተናግረዋል፣ ህብረተሰቡ ለበዓሉ  የገዛቸውን እንስሳት እንኳ ሳያርድ በሌሊት መፈናቀሉን ይናገራሉ።ሌላው በአምደወርቅ ከተማ የሚገኘውተፈናቃይም ህብረተሰቡ ወር ባልሞላ ውስጥ ለሁለት ጊዜ ተፈናቅሎ በችግር ላይ እንደሆነ አመልክተዋል። በዳሀና ወረዳ፣ተፈናቃዮች በበሽታና በረሀብ እየተሰቃዩ በመሆኑና የከፋ ነገር ከመድረሱ በፊት ወገን እንዲደርስለት ተፈናቃዮቹ ጥሪ አቅርበዋል።
ህፃናትና ወላዶች መኝታ የላቸውም፣ አቅመ ደካሞችም የወገንን ፈጣን ምላሽ እንደሚጠብቁ አመልክተዋል።የአማራ ክልለ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ተጠይቀው ተፈናቃዮችን ለማገዝ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል እርዳታ እናደርሳለን’’ ብለዋል።
በጦርነት ቀጣና ያሉ ወገኖች ለከፋ ርሀብ መጋለጣቸውን ጠቁመው ፣ ዓለም አቀፉ ረጂ ተቋማት መንገድ አስከፍቶ ሊታደጋቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአማራ ክልል ከወቅታዊው ጦርነት ጋር በተያያዘ 554 ሺህ ወገኖች መፈናቀላቸውንም አቶ ግዛቸው ገልጸዋል፡፡ የህዝቦችን ስቃይ ለማሳጠር ጦርነቱን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነውም ብለዋል፡፡ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከል ተጠሪ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መልካሙ ደስታን ተጨማሪ አስተያየት ለማካተት የባህርዳሩ ወኪላችን ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
ዓምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ