1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከምዕራብ ወለጋው ጭፍጨፋ የተረፉ ነዋሪዎች ምን ይላሉ?

ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2014

ባለፈው ቅዳሜ በታጣቂዎች በዘር ላይ ባነጣጠረው የጅምላ ግድያ የተጠቁና ከግድያው የተረፉ ተፈናቃዮች በከፋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስታወቁ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት ተፈናቃይ እንዳሉት እስካሁን የመንግስት የፀጥታ ኃይሎችን ተከትሎ የሚደረግ የአስከሬን ለቀማ እና ቀብር የመፈጸም ስራ እና ቁስለኞችን የማሳከም ስራ እተከናወነ ነው፡፡

https://p.dw.com/p/4D8wR
Äthiopien | 200 Zivilisten finden Zuflucht in der orthodoxen Kirche in Addis Abeba
ምስል Solomon Muchie/DW

ባለፈው ቅዳሜ በታጣቂዎች በዘር ላይ ባነጣጠረው የጅምላ ግድያ የተጠቁና ከግድያው የተረፉ ተፈናቃዮች በከፋ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ አስታወቁ፡፡ አስተያየታቸውን ለዶይቼ ቬለ የሰጡት ተፈናቃይ እንዳሉት እስካሁን የመንግስት የፀጥታ ኃይሎችን ተከትሎ የሚደረግ የአስከሬን ለቀማ እና ቀብር የመፈጸም ስራ እና ቁስለኞችን የማሳከም ስራ እተከናወነ ነው፡፡ 
ለዘለቄታው ግን ተስፋ እንደማይታያቸው የገለጹት አስተያየት ሰጪ ግድያው ከተፈጸመበት ከጊምቢ ወረዳው ቶሌ ቀበሌ የተፈናቀሉ ዜጎች አርጆ በምትባል ከተማ ብጠለሉም፤ እስካሁን ያገኙት ድጋፍ የለም፡፡ መንግስት በበኩሉ ግድያውን ተከትሎ በአከባቢው በታጣቂዎች ላይ እየወሰደ ያለው አፐሬሽን እየተሳካ መሆኑን እየገለጸ ነው፡፡ 
ሥዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ
 
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ