1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከመተከል ለተፈናቀሉ የሚሰበሰበው ገንዘብና እርዳታ 

ሰኞ፣ ጥር 24 2013

ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክልሉ ተፈናቃዩች የተላከው ድጋፍ  በአሶሳ ዞን ሆሞሻ በተባለ ወረዳ ተራግፎ የነበረና በቶሎ ተፈናቃዩች  አልደረሰም የሚል ቅሬታም ሲቀርብ የቆየ ሲሆን እርዳታው ከትናንት ጅምሮ ወደ ስፋራ ማጓጓዝ መጀመሩ ተገልጿል።በክልሉ 100,004 ተፈናቃዮች በተለያዩ ጣቢያዎች እንደሚገኙ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3ofcY
Äthiopien Ato Babekir  Halifa
ምስል Negassa Desalegn/DW

ከመተከል ዞን ለተፈናቀሉት መልሶ ማቋቋሚያ የሚሰበሰበው ገንዘብና እርዳታ 

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን  በተለያዩ ወረዳዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው በተለያዩ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉትን ዜጎች መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ  የሚያስችል ከ14 ሚሊዩን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን  በክልሉ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ  የተቋቋመው የገቢ አሰባሰብ አብይ ኮሚቴ አስታውቋል። የቤኒንሻጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው ገቢው የተሰበሰበው በክልል ደረጃ ካሉት ተቋማት እንዲሁም ከዞንና ወረዳ  ደረጃ ካሉት መስሪያ ቤቶች ነው። ከዚህ ቀድም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለክልሉ ተፈናቃዩች የተላከው ድጋፍ  በአሶሳ ዞን ሆሞሻ በተባለ  ወረዳ ተራግፎ የነበረና በቶሎ ተፈናቃዩች  አልደረሰም የሚል ቅሬታም ሲቀርብ የቆየ ሲሆን ከትናንት ጅምሮ ወደ ስፋራ ማጓጓዝ መጀመሩንም ገልጿል።

በክልሉ ውስጥ አንድ መቶ ሺ አራት  (100004) ዜጎች ተፈናቅለውበተለያዩ ጣቢያዎች እንደሚገኙ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኪሚሽን መረጃ ያመለክታል።በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ደረጃ ከግል ባለሀብቶችና ከመንግስት ተቋማት 50 ሚሊዩን ብር ለመሰብሰብ አቅደው በታህሳስ ወር መጨረሻ ወደ ስራ መገባቱን የክልሉ የግብርና ተፈጥሮ ሀብት ልት ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ሀሊፋ ለዲዳቢሊው (DW) ተናግረዋል፡፡  በክልሉ መተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ተፈናቃዩችን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት እስካሁን 14 ሚሊዩን ገንዘብ ከመንግስት ሰራተኞች መሰብሰቡን ጠቁመዋል፡፡ የገቢ ማሰባሰቡ ሂደት የክልሉን መንግስት እና በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶችን ያሳተፈ ሲሆን  ከ40 በላይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥያቄ ማቅባረቸውን አክልዋል፡፡
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽ ኮሚሽነር አቶ ታረቀኝ ታሲሳ በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ ከመቶ ሺ በላይ  ተፈናቃዩች በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ እንደሚገኙ ገልጸው  በተቀናጀ መልኩ በቅርበት አገልግሎት ለመስጠት በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማስባበሪያ ጽ/ቤት መክፈቱን ጠቁመዋል፡፡
በቤኒሻጉል ጉሙዝ በክልል ደረጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች ገቢ የማሰባሰብ ስራ ታህሳስ 23/2013 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን 12 ተቋማት ገቢ የማሰባሰብ ስራውን ይመራሉም ተብሏል። በዞኑ የተፈጠረውን የጸጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያግዛሉ የተባሉ የተለያዩ  እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነም የጸጥታ ስራውን የሚመሩት ሌቴናል ጀነራል አስራት ደነሮ ከዚህ ቀደም መናገራቸውን መዘገባችንም ይታወሳል።

Karte Äthiopien Metekel EN

ነጋሳ ደሳለኝ 

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ