1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር /ኦብነግ ከምርጫ ራሱን ማግለሉ

ቅዳሜ፣ መስከረም 8 2014

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር /ኦብነግ የሁለት ሳምንት ዕድሜ በቀረውና በሶማሌ ክልል በሚካሄደው ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታወቀ፡፡ የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ አብዱቃድር ሀሰን ለDW በስልክ በሰጡት መረጃ ፓርቲው ሁለት ሳምንት ከቀረው የሶማሌ ክልል ምርጫ በተለያዩ  ምክንያቶች ራሱን ማግለሉን ተናግረዋል፡፡

https://p.dw.com/p/40VBt
Mitglieder der ONLF/Ogaden National Liberation Front
ምስል Getty Images/A.Maasho

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር /ኦብነግ ከምርጫ ራሱን አገለለ

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር /ኦብነግ የሁለት ሳምንት ዕድሜ በቀረውና በሶማሌ ክልል በሚካሄደው ምርጫ እንደማይሳተፍ አስታወቀ፡፡ የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ አብዱቃድር ሀሰን ለDW በስልክ በሰጡት መረጃ ፓርቲው ሁለት ሳምንት ከቀረው የሶማሌ ክልል ምርጫ በተለያዩ  ምክንያቶች ራሱን ማግለሉን ተናግረዋል፡፡

“ከምርጫው ራሳችንን ያገለልንበት በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ በመጀመርያ ብዙ ጉድለቶች አሉ  በመራጮች አመዘጋገብ ፣ በመራጮች ካርድ ስርጭት ፣ እንዲሁም በወረዳ እና ክልል ደረጃ ያለው የምርጫ አሰራር ከገዢው ፓርቲ ጋር አሰራር ጋር ተቀላቅሏል፡፡ ስራዎቻቸውንና የስራ ፍሰቱ ላይ ምንም ቁጥጥር የለም፡፡በጣም ብዙ የአሰራር ስርዓት መጣስ አለ፡፡ ስለሶማሌ ክልል ምርጫ ህገወጥነት እና ጭፍን ሁኔታ ማውራት አስቸጋሪ ነው፡፡”

ፓርቲው ከምርጫው ራሱን ለማግለል ባቀረባቸው ምክንያቶች ዙርያ ከምርጫ ቦርድ ጋር ተነጋግሮ ስለመሆኑ የተጠየቁት ቃል አቀባዩ ለቦርዱ ቅሬታ ማቅረባቸውን ጠቅሰው ባነሷቸው ጉድለቶች ላይ ጉልህ ማስተተካከያ አለመደረጉን ጠቁመዋል፡፡

 “አዎን ከአምስት ወራት ቀደም ብሎ በሶማሌ ክልል የምንገኝሶስት አራት ፓርቲዎች ያለንን ቅሬታ በጋራ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ልከናል ፡፡ እነሱም የተወሰኑ አጣሪ ኮሚቴዎችን አስራ አራት በሚሆኑ የክልሉ ወረዳዎች በመላክ በርካታ ጥሰቶችን አግኝተዋል በዚህም ምርጫው ለወራት እንዲራዘም ውሳኔ አሰላፈዋል ፤ በዚያ ጊዜ ጉድለቶች ይስተካከላሉ የሚል እምነት ነበረን፡፡ ነገር ግን ከሶስት ወራት በኃላ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነበሩት ጉድለቶች ላይ ጉልህ ለውጥ ሳያደርግ በተመሳሳይ ሁኔታ ሒደቱ እንዲቀጥል አድርጓል፡፡ በመሆኑም ምርጫው ህወሀት ከሀያ አምስት አመት በፊት ሲካሂደው ከነበረው ምርጫ ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡”

የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግምባር /ኦብነግ በቀጣይ በሰላማዊ መንገድ እንደሚሰራ እና ለሶማሌ ህዝብ መብቶች መከበር እንደሚታገል የፓርቲው ቃል አቀባይ ለዶይቼ ቬሌ ገልፀዋል፡፡

“በቀጣይ በሰላማዊ መንገድ እንሰራለን ፣ ለሶማሌ ህዝብ መብቶች መከበር በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን፡፡ በኢትዮዮጵያ የሚገኙ ፓርቲዎች ውጥረት  እንዲሁም ጦርነትን አቁመው ወደ ውይይት በመግባት ለችግሩ መፍትሄ እንዲያመጡ  ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በኢትዮጵያ ብሄሮች መካከል ትልቅ ክፍተት አለ ፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ቡድኖች እርስ በእር አለመግባበት አለ ስለሆነም ወደ ውይይት መጥቶ መነጋገር እና ችግሮቻችንን መገንዘብ አለብን፡፡ በእውነቱ በሀገር ውስጥ ያለውን ችግር  ዝቅ አድርገን አንመልከትም ስለዚህ ችግሩን ለመፍታት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን፡፡”

ትክክለኛ ባልሆነ ምርጫ በመሳተፍ ህዝባችንን ማታለል የለብንም ስለዚህም ከምርጫው ራሳችንን ማግለላችን ተገቢ ነው ብለዋል የፓርቲው ቃል አቀባዩ፡፡

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ