1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ» ዘመቻ

ዓርብ፣ ግንቦት 13 2013

የምዕራቡ ዓለም ሃገራት ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙ የሚጠይቅ መልዕክት ማስጀመሪያ የተባለው  መርሃ ግብር ዛሬ አዲስ አበባ ተካሄደ። የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያንን ሉዓላዊነት የሚጋፋ እና አላስፈላጊ ጫናን የሚያሳድሩ የመንግስታት ውሳኔዎችን በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚቃወሙ መልእክቶችን ማስተላለፍ የንቅናቄው ዓላማ ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3tmcY
Äthiopien Addis Abeba | Proteste gegen die USA
ምስል Seyoum Getu/DW

የምዕራቡ ዓለም ሃገራት በኢትዮጵያ ጣልቃ አይግቡ ተብሏል

የምዕራቡ ዓለም ሃገራት ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙ የሚጠይቅ መልዕክት ማስጀመሪያ የተባለው  መርሃ ግብር ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሄደ። ፖለቲከኞች፣ አርቲስቶች፣ ሲቪክ ማህበራትና ታዋቂ የተሰማሩ ግለሰቦች የተሰባሰቡበትና ከመንግስት ተሳትፎ ውጭ ነው የተባለው የቡድኑ ተልእኮም የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያንን ሉዓላዊነት የሚጋፋ እና አላስፈላጊ ጫናን የሚያሳድሩ የመንግስታት ውሳኔዎችን በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚቃወሙ መልእክቶችን ማስተላለፍ የንቅናቄው ዓላማ ነው ተብሏል። የንቅናቄውን ሐሳብ የጠነሰሱና የሚመሩት የስብስቡ አባላት ዛሬ አዲስ አበባ ፒያሳ አከባቢ በሚገኘው የሐገር ፍቅር ቲያትር ተገኝተው መፈክሮችን በማሰማት መልእክትም አስተላልፈዋል። ከቡድኑ አባላት አንዱ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ማብራሪያም የመርሃግብሩ ዓላማ  ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ሃገራትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም «እጃችሁን ከኢትዮጵያ ላይ አንሱ» በሚል መሪ ሐሳብ በያሉበት ሆነው ለአንድ ሰዓት መልዕክታቸውን እንዲያስተላልፉ ነው ብለዋል። «ብሔራዊ ክብር በሕብር» የሚል ስያሜ ያለው መርሃ ግብሩ ዛሬ ይጀመር እንጂ ቀጣይነት ያለው መሆኑንም ኮሚቴው ዐሳውቋል። በኮቶቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የህግና ታሪክ ተመራማሪው ዶ/ር አልማው ክፍሌ እንደሚሉት ግን መሰል ተዕእኖዎችን የሚከተሉ ፈተናዎችን ለመቀነስ መንግስት ዲፕሎማሲ ላይ ጠንከር ያለ ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋ።

ሥዩም ጌቱ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ