1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስር ላይ የነበሩ የቀድሞ ባለሥልጣናት መለቀቅ

ዓርብ፣ መጋቢት 6 2016

የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር በቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና የቀድሞ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አብዲ መሓመድ ዑመር ላይ ቀርቦ የነበረ ክስ ማቋረጡ አስታወቀ። ፍትሕ ሚኒስቴር ክሱን ያቋረጠው "ለህዝብ ጥቅም ሲባል" መሆኑ ገልጿል። በተለያዩ ክሶች፥ በሙስና ወንጀል ክስ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሲታይ የነበር

https://p.dw.com/p/4df1n
Äthiopisches Justizministerium
ምስል Solomon Muchie/DW

እስር ላይ የነበሩት የቀድሞ ባለስልጣናት መለቀቅ

እስር ላይ የነበሩ የቀድሞ ባለሥልጣናት ክስ መቋረጡ  

የኢትዮጵያ ፍትሕ ሚኒስቴር በቀድሞ የሜቴክ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና የቀድሞ የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አብዲ መሓመድ ዑመር ላይ ቀርቦ የነበረ ክስ ማቋረጡ አስታወቀ። ፍትሕ ሚኒስቴር ክሱ ያቋረጠው "ለህዝብ ጥቅም ሲባል" መሆኑ ገልጿል። የኢትዮጵያ ፍትህ ሚኒስቴር ትላንት ማምሻው እንዳለው ከ2011 ዓመተምህረት ጀምሮ ሂደት ላይ የቆየው በቀድሞው የሜይቴክ ሐላፊ የሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና በቀድሞው የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አብዲ መሓመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) ቀርበው የነበሩ ክሶች ለህዝብ ጥቅም ሲባል ማቋረጡ አስታውቋል። 
በእነ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው መዝገብ ስር ያሉ የተለያዩ ክሶች፥ በሙስና ወንጀል ክስ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድቤት ሲታይ የነበረ ሲሆን፥ የእነ አብዲ መሓመድ ዑመር (አብዲ ኢሌ) ክስ ደግሞ ለዓመታት በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድቤት የሕገመንግስት እና የሽብር ወንጀል ጉዳዮች ችሎት የክርክር ሂደት ላይ የቆዩ መሆናቸው ተጠቅሷል። ለዶቼቬለ የተናገሩት የቀድሞው የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ)ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው የሕግ ጠበቃ አቶ ሃፍቶም ከሰተ፥ ደንበኛቸው ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ግዜ ድረስ ከእስር ባይለቀቁም፥ ፍትሕ ሚኒስቴር ክሱን ማንሳቱ እና ፍርድቤትም ጥያቄ ተከትሎ ከእስር እንዲለቀቁ ትእዛዝ መፃፉ ነግረውናል።
በደንበኛቸው ላይ ለዓመታት አለአግባብ እንግልት መፈፀሙ የሚገልፁት ጠበቃ ሃፍቶም ከሰተ፥ የቀረቡባቸው ክሶችም በግዜ ሂደት ልክ እንዳልሆኑ እያሳየን መጥተናል ብለዋል። በሌላ በኩል "አብዲ ኢሌ" በሚለው ቅፅል ስም የሚታወቁት የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድር አብዲ መሓመድ ዑመር የጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ ወይም የእርስ በርስ ግጭት በማስነሳት በመንግስት ተከሰው የነበረ ሲሆን፥ የነበረ ክስ ተቋርጦ ትላንት ማምሻው ከእስር መለቀቃቸው ያረጋገጡልን ደግሞ ጠበቃቸው አቶ አስክንድር ገዛህኝ ናቸው። ጠበቃ እስክንድር "ትላንትና ወደ አመሻሹ አካባቢ ከማረሚያ ቤት ወጥተው፣አሁን ከቤተሰብ ጋር ነው የሚገኙት" ሲሉ ለዶቼቬለ ገልፀዋል።

ሚሊዮን ኃይለሥላሴ 
አዜብ ታደሰ 
ዮኃንስ ገብረእግዚአብሔር