1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 72 ሰዎች የሞቱበት የግሬንፊል አደጋ ሁለተኛ አመት ተዘከረ 

ቅዳሜ፣ ሰኔ 8 2011

ከሁለት አመታት በፊት በለንደን የግሬንፊል የመኖሪያ ሕንፃ ላይ ከተነሳው የእሳት ቃጠሎ የተረፉ ነዋሪዎች እና የሟቾች ቤተሰቦች አሰቃቂው አደጋ የደረሰበትን ሁለተኛ አመት በትናንትናው ዕለት አስበዋል።

https://p.dw.com/p/3KWZG
Grenfell Tower Jahrestag Gedenken
ምስል Reuters/P. Nicholls

በቃጠሎው 72 ሰዎች ሲሞቱ 70 ቆስለዋል

ከሁለት አመታት በፊት በለንደን የግሬንፊል የመኖሪያ ሕንፃ ላይ ከተነሳው የእሳት ቃጠሎ የተረፉ ነዋሪዎች እና የሟቾች ቤተሰቦች አሰቃቂው አደጋ የደረሰበትን ሁለተኛ አመት በትናንትናው ዕለት አስበዋል። በምዕራባዊ ለንደን በሚገኘው የመኖሪያ ሕንፃ ላይ የተነሳው ቃጠሎ በአጠቃላይ የ72 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። ሌሎች 70 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በቃጠሎው ሕይወታቸውን ካጡ 72 ሰዎች መካከል ዘጠኙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ናቸው። 223 የሕንፃው ነዋሪዎች ከቃጠሎው ተርፈዋል። 
ሐና ደምሴ
እሸቴ በቀለ