1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«ኢትዮጵያዊነት በተግባር» የርዳታ ማኅበር

ሐሙስ፣ ጥቅምት 1 2011

ኢትዮጵያዊነት በተግባር የተሰኘ የበጎ አድራጎት ማኅበር በኢትዮጵያ ዉስጥ በተለይ ተፈናቃዮችንና ችግረኞችን በመርዳት ላይ እንደሆነ ባወጣዉ መግለጫ አመለከተ። «በሀገሪቱ ወቅታዊና አንገብጋቢ ርዳታ የሚያስፈልግባቸዉ ቦታዎችን አስሰን በመድረስ ድጋፍ እናደርጋለንም» ሲል ማኅበሩ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/36EhH
20.06.2013 DW Online Karten Basis Aethiopien spanisch

«በሀገራችን የተለያዩ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮች በመደቀናቸዉ በምንችለዉ ዘርፍ ሀገራችንን እንረዳለን» ሲል የጠቀሰዉ ማኅበሩ፤ በተለይ በአሁኑ ወቅት ለተፈናቃዮች የርዳታ እጁን እንደዘረጋ ነዉ የተገለፀዉ። ኢትዮጵያዊነት በተግባር  በካናዳ፤ በአሜሪካ፤ በአዉሮጳ ፤ በመካከለኛዉ ምሥራቅ እንዲሁም በአፍሪቃ ዉስጥ የተለያዩ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነም « DW» ያነጋገራቸዉ በበርሊን ከተማ የማኅበሩ አባልና ተጠሪ ተናግረዋል። በበርሊን ነዋሪ የሆኑት የማኅበሩ ተጠሪ ወ/ት ሰብለ ወንጌል ዓለምሰገድን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል አነጋግሮ አጠር ያለ ዘገባ ልኮልናል። 


ይልማ ኃይለ ሚካኤል 
አዜብ ታደሰ 
አርያም ተክሌ