1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በኢትዮጵያ የተቋረጠውን የፀረ ኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ ሊቀጥል ነው

ሐሙስ፣ ሐምሌ 1 2013

ዶክተር ሙሉቀን ዩሐንስ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባትን ፍትሃዊ ሥርጭት ለማረጋገጥ ከሚሰራው ከኮቫክስ ከምታገኘው በተጨማሪ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የአስትራዜኒካ እንዲሁም የጆንሰንና ጆንሰን ክትባቶችን ለመግዛት አቅዳለች። የሦስተኛው የወረርሽኜ ማዕበል ስጋት ስላለ ሕዝቡ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል።

https://p.dw.com/p/3wDV1
Äthiopien | Muluken Yohannes
ምስል Privat

የፀረ ኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ

ኢትዮጵያ በአቅርቦት እጥረት ምክንያት የተጓጎለውን የፀረ ኮቪድ ክትባት ዘመቻ ለመቀጠል ተጨማሪ 400 ሺህ ክትባቶችን ነገና ከነገ በስትያ ወደ ሃገር ውስጥ ልታስገባ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ።.በሚኒስቴሩ የክትባት ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዩሐንስ በተለይ ለዶይቸ ቬለ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ፣ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባትን ፍትሃዊ ሥርጭት ለማረጋገጥ ከሚሰራው ከኮቫክስ ከምታገኘው በተጨማሪ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የአስትራዜኒካ እንዲሁም የጆንሰን እና ጆንሰን ክትባቶችን ለመግዛት አቅዳለች። ሦስተኛው የወርሽኙ ማዕበል ይከሰታል የሚል ስጋት ስላለም ሕብረተሰቡ ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርግ  ከፍተኛ አማካሪው አሳስበዋል።
ታሪኩ ኃይሉ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ