1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ አስትራዜኒካ ክትባት መስጠቷን ትቀጥላለች

ረቡዕ፣ መጋቢት 8 2013

ኢትዮጵያ አስትራዜኒካ የተሰኘውን የኮቪድ - 19 ክትባት መስጠቷን እንደምትቀጥል የጤና ሚኒስቴር ዐስታወቀ። በርካታ የአውሮጳ ሃገራት ክትባቱ ተያያዥ ጠንቆች አሉት በሚል መስጠት አቊመዋል።

https://p.dw.com/p/3qlVZ
Coronavirus Impfstoff Symbolbid
ምስል picture-alliance/Flashpic

ክትባቱ እንዲቆም እስካልወሰነ ድረስ ክትባቱ ይሰጣል

ኢትዮጵያ አስትራዜኒካ የተሰኘውን የኮቪድ - 19 ክትባት መስጠቷን እንደምትቀጥል የጤና ሚኒስቴር ዐስታወቀ። በርካታ የአውሮጳ ሃገራት ክትባቱ ተያያዥ ጠንቆች አሉት በሚል መስጠት አቊመዋል። ኢትዮጵያ ክትባቱን በሚመለከተው የጥራት ተቆጣጣሪ አካል አስፈትሻ ማስገባቷን እና የጤና ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ማረጋገጫ ሰጥቶ ክትባቱ እንዲቆም እስካልወሰነ ድረስ ክትባቱ ይሰጣል ተብሏል። 

ብዙ የአውሮጳ አገራት አስትራዜኒካ የተባለው የኮቪድ - 19 የክትባት ደምን የማርጋት ተጓዳኝ የጤና ጠንቅ አስከትሏል በሚል ጥቅም ላይ እንዳይውል እግድ ጥለውበታል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በተለይ በክትባቱ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የጤና ባለሙያዎቿን በቀጣዮቹ ከሰባት እስከ አሥር ቀናት ውስጥ ከትባ እንደምታጠናቅቅ አረጋግጣለች።

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ