1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ አሜሪካ በምታስተናግደው በሕዳሴ ግድብ ውይይት ትሳተፋለች ተባለ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 20 2012

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዜጋ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በዲፕሎማሲ ላይ በማተኮር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጠዉ መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ የሦስቱንም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት መጥራቷን መናገራቸዉ ተመልክቶአል።

https://p.dw.com/p/3SHK0
Äthiopien | Außenministeriums-Sprecher Nebyat Getachew
ምስል DW/G. T. Hailegiorgis

ኢትዮጵያ በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ዩናይትድ ስቴትስ በምታስተናግደው የሦስትዮሽ ውይይት ላይ እንደምትሳተፍ አስታውቃለች፡፡ ይህ የተነገረዉ ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዜጋ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በዲፕሎማሲ ላይ በማተኮር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዛሬ በሰጠዉ መግለጫ ላይ ነዉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢያት ጌታቸው ዛሬ ይፋ ባደረጉት መግለጫ ዩናይትድ ስቴትስ የሦስቱንም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት መጥራቷን መናገራቸዉ ተመልክቶአል። በሌላ በኩል ቃል-አቀባዩ  ቀጣዩ የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ እንዲሆኑ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኃሳብ ማቅረባቸው  እና በቀጣይ ይኸዉ ሃሳብ ይረጋገጣል ብለዋል። ወደ 400 ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያዉያን በሊባኖስ እንደሚኖሩ የገለፁትና፤ መንግሥት በዜጎች ላይ የሚደርሰዉን የመብት ጥሰት ጥቃት ለመከላከል እየሰራ ነዉ ፤ ዜጎችንም ወደ ሃገር ለመመለስ እየተሰራ ነዉ ብለዋል። 400 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሊባኖስ ውስጥ እንደሚገኙ የገለፀዉ መግለጫዉ ፤ መንግሥት የዜጎቹን ጉዳይ የሚከታተል ልዑክ ወደ ሊባኖስ እንደሚልክ አስታዉቀዋል። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል።


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 


ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ