1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ፦ በግጭት ጦርነቱ የሰላማዊ ዜጎች መብት ጥሰት

እሑድ፣ መስከረም 1 2015

ኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት ጦርነቱ የተነሳ ሰላማዊ ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ አሰቃቂ በሆነ መልኩ ሲገደሉ፤ ጥቃት ሲደርስባቸው እና በገፍ ሲፈናቀሉ ይታያል። በግጭት ጦርነቶች ወቅት የሰላማዊ ዜጎች የሰብአዊ መብት አጠባበቅ» ምን ይመስላል? የሰብአዊ መብት ተሟጋች ባለሞያዎችን ለውይይት ጋብዘናል። ሙሉው ውይይት ከታች በድምፅ ይገኛል።

https://p.dw.com/p/4GeL0
Tigray-Krise in Äthiopien
ምስል Eduardo Soteras/AFP

«ማጠንጠኛው ተጠያቂነት ነው» የእንወያይ መሰናዶ

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደ ጎርጎርጎሪዮስ አቆጣጠር በ1948 የጸደቀው የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ (UDHR) ሠነድ የሰብአዊ መብቶች በየትኛውም ቦታ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ያሳስባል። ሠነዱ ከጸደቀ አንድ ምእተ ዓመት ሊሞላው ጊዜው እየገሰገሰ ነው። ዛሬም ድረስ ግን ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለማችን የተለያዩ ቦታዎች የሰብአዊ መብቶች ሲጣሱ ብሎም ሲደፈለቁ ይታያል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎችም በጦር መሣሪያ ግጭቶች መከራቸውን ማየታቸውን ቀጥለዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ «በግጭት ጦርነቶች ወቅት የሰላማዊ ዜጎች የሰብአዊ መብት አጠባበቅ» ምን ይመስላል? የዛሬው ውይይት በዋናነት ከሚያተኩርባቸው ነጥቦች አንዱ ነው። በውይይቱ እንዲሳተፉ ሦስት እንግዶችን ጋብዘናል። የውይይቱ ተሳታፊዎች፦

1-አቶ መስዑድ ገበየሁ፦ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ሕብረት ዋና ሥራ አሥኪያጅ

2-አቶ ፍስሓ ተክሌ፦ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ቀንድ የሰብአዊ መብቶች አጥኚ

3-አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ሥራ አሥኪያጅ ናቸው።  

ሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሕግጋት አንጻር እንዴት ይታያሉ? ጥፋት አድራሾቹስ ምን አይነት ቅጣት ይጠብቃቸዋል? በግጭትም ሆነ ጦርነት ውስጥ ተሳታፊ ያልሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚከሰቱ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እንዴት መከላከል ይቻል? የሚሉ እና ሌሎች ጥያቄዎችም በውይይቱ ተነስተዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ