1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ በመንታ መንገድ የተሰኘዉ ጉባዔ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 28 2014

ኢትዮጵያ በመንታ መንገድ በተሰኘ ርዕስ  ትናንት በበየን መረብ ውይይት ተካሂዷል። ውይይቱ የተዘጋጀውና የተመራው በሁለት የአውሮጳ ፓርላማ አባሎች ሚሼሌ ሪቫዚ ከአረንጓዴዎቹ ወገን እና ያን ክሪስቶፍ ከለዘብተኞቹ በኩል ናቸው። 

https://p.dw.com/p/43xYu
Karte Sodo Ethiopia ENG

የጉባዔዉ መሪዎች ሁለት የአዉሮጳ ፓርላማ አባላት ናቸዉ

ከተጋባዥ ተናጋሪዎቹ አንዱ የሆኑትና በአውሮጳ የኢትይጵያውያን መድረክ ድልድይ ፕሬዝዳንት አቶ አበራ የማነአብ የጦርነቱን መነሻ ሲያስረዱ በመጅመሪያ ድምጽ ይህ ጦርነት በዴሞክራሲያዊ አግብብ በተመረጠ  መንግሥትና በአንድ የክልል ፓርቲና ለ27 ዓመትት በሥልጣን ላይ ቆይቶ በአገሪቱ ሕግ መሰረት ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ አላስረክብም ባለ የክልል ፓርቲ መካከል መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል። 

ዶክተር ዐቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ እስረኖችን በመፍታትና በስደት ላይ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በመጋበዝ  የፖለቲካ ምህዳሩን እንዲሰፋ በማድረግ፤ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረውን ጥሩ ያሆነ ግንኑኙት  በማሻሻል በርክታ የማሻሻያ ፕርግራሞችን ሲያስጀምሩና ሌላ አዲስ ፓርቲም ሲመሰርቱ  ህወሃት ወደ ክልሉ ዋና ከተማ በመሄድ ተቃውሞ ሲያካሂድ መቆየቱን አውስተው፤ በመጨርሻም ትቅምት 24 በስሜን እዝ ላይ ጣቅት ፈጽሟል ብለዋል። በትግራይ ቴሌቪዝን ወጥተቶ መግልጫ የሰጠውን አቶ ሴኩቲሬ ጌታቸውን በመጥቀስ በሆላንድ የቲልቡርግ ዩንቭርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ፕሮፈሰር ሚሪም ቫን ሬሰን በበኩላቸው በዚህ ጦርነት ኤርትራ ዋና ተዋናይ ናት በማለት ህወሃትን ለመውጋት ፕሬዝዳንት ኢሳይያስና ዶክተር ዐቢይ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል። በሳቸው አስተያየት ጦርነቱ የተጀመረውም የፌደራል መንግሥቱ የክልሉን ባለሥልጣኖች ለማሰር ጥቅምት 23 ልዩ ኃይል በላከ ግዜ ነው።

የባዚሊ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ቤት  ዳይሬክተር የሆኑት ወይዘሪት  አን ፊትዝ ጌላድ ግን ጥናታቸው የሚያሳየው የፌደርል መንግሥቱና የህወሃት ቅራኔ  የተፈጠረው የኢትዮጵያ መንግሥት ምርጫውን በማስተተላለፉ መሆኑን አውስተው፤ በስሜን ዕዝ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የጦርነቱ ጅማሮ መሆኑን እንዲሁም በጥቃቱ የሞቱትንና የጠፉትንም አሀዝ ጭምር በመግለጽ አስረድተዋል። የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት የምርጫውን መተላለፍ ቢቃወምም ይህ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተደረገ እንዳልነበረም አስረድተዋል። በዓለም ዙሪያ  በኮቪድ ምክንያት 78 አገሮች ልዩ ልዩ ምርጫዎችን አስተላለፈው ነበር በማለትም የኢትዮጵያው ምርጫ መተላለፍ የተለየ ሊሆን የማይገባው እንድነበር አስተድተዋል።

በጌንት ዩንቨርስቲ ፕሮፌሰር የሆኑት  ፕሮፌሰር ያን ኒሰን በበኩላቸው ከትግራይ ጋር ያላቸው ግንኑነት ከ198ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ በሥራ ምክኒያት መሆኑን አውስተው፤ ከመቀሌ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር የሠሯቸው የአፈርና ውሀ ጥበቃ ፕሮጀክቶች በጦርነቱ ምክንያት እንደወደሙና ህዝቡም ለረሀብ እንደተጋለጠ አስረድተው ጦርነቱ ቆሞ በመልሶ ግንባታው ሂደት ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።

መዓዛ ግደይም በበኩሏ በተለይ በሴቶች ላይ የደረስውን ጉዳትና ጥቃት ሰፋ አድርጋ በንግግሯ አስረድታለች። መአዛ የኢትዮጵያ ሰብአዊ ኮሚሽንን ገለልተኝነ ጥያቄ ውስጥ ያስገባች ሲሆን በትግራይ ቴሌቪዥን ጥቃት መፈጸሙን ያመኑት አቶ ሴኩቲሬ ጌታቸው የህወሃት  አመራር አይደሉም ስትልም አስተባብላለች።  የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ተወካይ ወይዘሪት አልባብ ተስፋየ ግን ኮሚሽኑ ገልለተኛ ስለመሆኑ የሠራቸውን እና እየሠራቸው ያሉትን የምርመራ ሥራዎች ማሳያዎች መሆናቸውን ገልጻለች።

በላይደን  ዩንቨርስቲ የአፍርካ ፖለቲካ ፕሮፊሰር  የሆኑት ፕሮፌሰር ያን ዓቢንክ በንግግራቸው ያተኮሩት በተለየ ሁኒታ መገናኛ ብዙሃን ትርክቶችን በማዛበትና በማጋነንም ጭምር ጦርነቱን  እያባባሱት መሆኑን፤ በቅርቡም  ቢቢሲ ገበሬዎችን ለመርዳት ትምህርት ቤቶች ለቀናት እንዲዘጉ መደረጉን፤ ኢትዮጵያ ለጦርነቱ ዝግጅት ትምህርት ቤቶችን ዘጋች በማለት መዘገቡን ጠቅስዋል። ህወጋት ታዳጊ ወጣቶችን በጦርነት ማሰለፉ የታወቀ ቢሆንም፤ መገናኛ ብዙሃኑ  ግን  ሲዘግቡ አይሰሙም በማለትም ተችተዋል። የአውሮጳ ሕብረት ለአፍሪቃም ሆነ ለኢትዮጵያው ግጭት ነጻና የማንም ተቀጽላ የሆነ ፖሊሲ ሊኖረ እንደሚገባም ፕሮፈሰሩ አሳስበዋል።

 የአውሮፓ ሕብረት  የአፍሪቃ ቀንድ ተወካይ  ወይዘሮ አኔተ ቬበር  ባሰሙት የማጠቃለያ ንግግር  የቀረቡት አስተያየቶችና ጥናቶች የተለያዩ ቢሆኑም ጠቃሚዎች መሆናቸውን አውስተው፤ ሕብረቱ ሰላም እንዲሰፍን  ከአፍርቃ ሕብረት ጋር መሥራቱን እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።  ስብሰብውን በመላው ዓለም ከ400 በላይ ተስተፊዎች በብይነ መረብ እንደተከታተሉት ታዉቋል።

 

ገበያዉ ንጉሤ

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ