1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ሰላም ለማንጣት ፍላጎት አላት ተባለ

ዓርብ፣ ሰኔ 3 2014

የአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ሕወሓትንና የፌዴራል መንግሥትን ማደራደር ጀምረው እንደሆን በ DW የተጠየቁት አምባሳደር ዲና ኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት ፍላጎት እንዳላት ከመግለፅ በዘለለ ግልጽና የተብራራ ምላሽ አልሰጡበትም።

https://p.dw.com/p/4CXAv
Äthiopien l Sprecher des Außenministeriums - Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

ሳምንታዊዉ የዉጭ ጉዳይ ሚ/ር መግለጫ

ኢትዮጵያ ከአረብ አገሮች ጋር ባላት ግንኙነት ውስጥ "ይሄ ተቀይሯል የሚባል ነገር የለም" ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ። የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ይህንን ያሉት ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ኢትዮጵያ ከአረቡ ዓለም አገራት ጋር መስርታው የነበረው ምልካም ግንኙነት መሻከር ውስጥ ገብቷል ስለመባሉ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ነው። ይሁን እንጂ "ችግሮች አሉ" ያሉት ዲና አንዱ ችግርም ከህዳሴ ግድብ ግንባታ ጋር የተገናኘ መሆኑን ጠቅሰዋል።ኢትዮጵያ በበርበራ ወደብ ላይ የነበራትን ድርሻ ስለማጣቷ ለቀረበላቸው ጥያቄ የተጣራ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

የአፍሪካ ቀንድ የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ ሕወሓትንና የፌዴራል መንግሥትን ማደራደር ጀምረው እንደሆን በ DW የተጠየቁት አምባሳደር ዲና ኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት ፍላጎት እንዳላት ከመግለፅ በዘለለ ግልጽና የተብራራ ምላሽ አልሰጡበትም።

ኢትዮጵያ ሱዳን በኃይል የያዘችባትን መሬት በተመለከተ "ሁኔታውን ላለማባባስ ብልጠት የተሞላበት አካካሄድ እየተከተለች" መሆኑን ገልፀው ወደ ግጭት ውስጥ አለመግባቷ ስኬት እንደሆነና ሱዳን አሁንም ቢሆን ከዚያ ድርጊቷ ትቆጠባለች በሚል መንግሥት የሰላምን አማራጭ እያራመደ መሆኑን ቃል ዐቀባዩ ተናግረዋል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ